ባለሥልጣኑ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የዲስፕሊን ኮሚቴዎች ስልጠና ሰጠ ።
ባለሥልጣኑ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የዲስፕሊን ኮሚቴዎች ስልጠና ሰጠ ።
መስከረም 14/2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ከማዕከል አስከ ወረዳ ለሚገኙ የዲስፕሊን ኮሚቴዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል ።
ስልጠናውን የሰጡት የባለሥልጣኑ የስነምግባርና ጸረ ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ ተቋሙ የተሰጡትን ግዴታዎችና ኃላፊነቶች ሲወጣ አንዳንድ ጊዜ ለብልሹ አሰራር የመጋለጥ እድሉ ያለው በመሆኑ፣ አመራሩ፣ ባለሙያውና በተለይም የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በታማኝነት፣ በፍትሃዊነትና ሚስጥር በመጠበቅ ህዝብን ማገልገል ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የዲስፕሊን ኮሚቴዎች የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችን የስነ-ምግባር መመሪያ ቁጥር 3/2015ን መሠረት በማድረግ ህጋዊና ገለልተኛ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥቶዋል።
የዲስፕሊን ኮሚቴዎች ከጥቅም ግጭት የጸዱ፣ ገለልተኛ፣ የተከሳሽን የመደመጥ መብት የሚያከብሩና በምርመራ ወቅት ሚስጥር የሚጠብቁ መሆን እንዳለባቸው አቶ እዮብ ከበደ ያሳሰቡ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ከተሰጠው ተልዕኮ አንጻር ተቋሙን ከብልሹ አሰራር የጸዳ ለማድረግ የቁጥጥርና የመከላከል ስራው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።
መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments