ባለስልጣኑ የጎቤና ሸኖዬ የወጣቶች ባህላዊ ጭፈራ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የጎቤና ሸኖዬ የወጣቶች ባህላዊ ጭፈራ ትወፊቱን በጠበቀ መልኩ አከበረ

ባለስልጣኑ የጎቤና ሸኖዬ የወጣቶች ባህላዊ ጭፈራ ትወፊቱን በጠበቀ መልኩ አከበረ

​              መስከረም 12/2019 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኦሮሞ ሕዝብ ባሕላዊ መገለጫ የሆነውን የወጣቶች ክብረ በዓል "ጎቤና ሺኖዬ" ባሕላዊ እሴት ትውልድ የሚገነባበትና ለቀጣይ ማሕበራዊ ሀላፊነት በሚያበቃ ሥነ-ሥርዓት በድምቀት አክብሯል።

​የ"ጎቤና ሺኖዬ" ክብረ በዓል የክረምት ወቅት አልፎ የበጋ ወቅትን በደስታና በፍቅር ለመቀበል ወጣቶች ተሰባስበው ከሳምንት በላይ የተለያዩ ባሕላዊ ጨዋታዎችን በአንድነትና በነጻነት የሚከውኑበት ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ነው።

​ባለስልጣኑ በበዓሉ አከባበር ወቅት ባዘጋጀው ልዩ መድረክ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ ለማስጠበቅ ደንብ ማክበርን የህብረተሰቡ ባህል ለማድረግና የደንብ መተላለፎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰጥቷል።

​ባህላዊ እሴቶችን ማጎልበትና መጠበቅ እንደሚገባ ሁሉ፣ ህግና ደንብን ማክበርም የአንድ የሰለጠነ ማህበረሰብ መገለጫ በመሆኑ ወጣቶች የከተማዋን ደንብና ስርዓት በማስከበር ረገድ የጎላ ድርሻቸውን እንዲወጡ በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።

​መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments