የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ለህዝባዊ አመኔታ" በሚ...

image description
- In code inforcement    0

የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ለህዝባዊ አመኔታ" በሚል መሪ ቃል የፖናል ውይይት ተካሄደ።

የላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ለህዝባዊ አመኔታ" በሚል መሪ ቃል የፖናል ውይይት  ተካሄደ።

                 ጷጉሜ 05/2018 ዓ.ም
                **አዲስ አበባ**

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ፍትሐዊ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትን በመዘርጋት የዜጎችን እንግልት መቀነስ፣ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎትን ማረጋገጥ እና የሕዝብ አመኔታን ማጠናከር የሚያስችል የፓነል ውይይት መድረክ ከአመራሮችና ሰራተኞች ጋር አካሂዷል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ለመላው የመዲናችን ነዋሪዎች እና ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአዲሱ ዓመት የላቀ አገልግሎት በመስጠት የህዝብ አመኔታን የምናጎለብትበት እና መዲናችን አዲስ አበባን ይበልጥ የጸዳች፣ ውብና ከደንብ መተላለፍ የጸዳች ለማድረግ በቅንጅት በመስራት ስኬት የምናስመዘግብበ ይሆናል ብለዋል።

​የአገልግሎት አሰጣጥ ወቅታዊ ሁኔታ፣ የተገኙ ስኬቶችና የታዩ ክፍተቶች በስፋት የተገመገሙ ሲሆን፣ በተለይም የመንግስት አገልግሎቶችን ከወረቀት አሰራር ወደ ዲጂታል ማዕቀፍ በማሸጋገር ረገድ ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን የመወያያ ሰነዱን ያቀረቡትየባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት፣ አገልግሎት አሰጣጥድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀጸላ ገልጸዋል ።

​አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝ ማድረግ እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር መገንባት እንደሚያስፈልግ በሰነዱ ተገልጿል ።

የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ከሰራተኞች ከፍተኛ የሞራል ዲስፕሊን፣ አገልጋይነት፣ ታማኝነትና የህዝብን አደራ በቅንነት መወጣት የሚጠበቅ ሲሆን ከአመራሩ በኩል ደግሞ አርአያነት ያለው አመራር መስጠት፣ የሰራተኛውን አቅም መገንባትና የዜጎችን ቅሬታ በቅርበት መፍታት እንደሚገባ ተመላክቷል።

በመድረኩ የባለስልጣኑ አመራሮችና ዳይሬክተሮች ለጶጉሜ 5 የነገ ቀንና ለ2019 አዲስ አመት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

​መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments