መጪው የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል የደመራ እና የ...

image description
- In code inforcement    0

መጪው የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል የደመራ እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

መጪው የዘመን መለወጫ፣ የመስቀል የደመራ እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

               4/13/2018 ዓ.ም
              **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን መጪው የዘመን መለወጫ ፣የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ለአመራሮቹ እና ለአባላቱ የስራ ስምሪት ሰጠ።

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የዘመን መለወጫ ፣መስቀልና ኢሬቻ በዓላት በዓለም የማይዳሰስ ቅርስ የተመዘገቡና በከተማችን የመተሳሰብ፣ የአብሮነት፣የአንድነት በዓላት እንደመሆናቸው ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴትቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከህብረተሰቡ ጋር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሊሰራ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል ።

በስምሪቱ የክፍለ ከተሞች አስተባባሪዎች ከወረዳ አመራርና አባላቸው ጋር  በመናበብ በዓሉ በሚከበርበት ወቅት በከተማዋ ላይ የተሰሩትን  መሰረተ ልማቶች እንዳይበላሹ ህብረተሰቡ በመቀናጀት ከፀጥታ አካላት ጋር በመናበብ ከተማችንን ጽዱ እና ውብ እንድትሆን መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል ።

በበዓላት ወቅት ሊፈጸሙ የሚችሉ የደንብ መተላለፎችና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዳይኖሩ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅና በበዓሉን አስመልክቶ የሚደረጉ ህገወጥ የእንስሳት እርድ ፣አላሰፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖርና የግባእት እጥረት እንዳያጋጥም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የመረጃ ልውውጥ እየተደረገ በሆኑ በመግለፅ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በዓሉን አስመልክቶ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችና ሌሎች የደንብ መተላለፎች እንዳይከሰቱ  ቅድመ ዝግጅት ማድረግ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚፈጸሙ የደንብ ጥሰቶችን ህጋዊ እርምጃ የመውሰድ ተግባርን በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments