ባለስልጣኑ የንግድ ተቋማት ለማህበረሰቡ በምሽት...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የንግድ ተቋማት ለማህበረሰቡ በምሽት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እዳለባቸው ገለፀ

ባለስልጣኑ የንግድ ተቋማት ለማህበረሰቡ በምሽት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እዳለባቸው ገለፀ
   
              ነሐሴ/21 /2018 ዓ.ም
                 አዲስ አበባ

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከከተማው ንግድ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በጉለሌ ክፍለ ከተማ መጪውን በዓላት አስመልክቶ የንግድ ተቋማት በምሽት ክፍለ ጊዜ ለህብረተሰቡ አስፈላጊውን አገልግሎት መስጠት እዳለባቸው  ገለፀ።

ባለስልጣኑ  ቅንጅታዊ ስራ ህብረተሰቡ የበዓል ገበያውን በፍላጎቱና በተረጋጋ ሁኔታ መሸመት እንዲችል የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያለመ ሲሆን በተለይም በምሽት ሰዓት ህዝቡ ያለምንም እንግልት ሸቀጦችንና አገልግሎቶችን ማግኘት የሚችልበት አሰራር እሰሸከ ምሽቱ 4 ሰዓት አገልገሸሎት መስጠት እንዳለባየው ገልጿል።

በምሽት ንግድ ወቅት የሚስተዋሉ ህገ-ወጥ የዋጋ ጭማሪዎችን፣ በህገ-ወጥ ቦታዎች ላይ የሚከናወኑ ንግዶችንና የህዝብና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴን የሚያደናቅፉ ደንብ መጣሶችን የመከላከልና የማስተካከል እርምጃዎች የሚወሰዱ ይሆናል።

​ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከከተማው ንግድ ቢሮና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የጀመረውን የተቀናጀ የደንብ ማስከበርና የቁጥጥር ስራ አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ህብረተሰቡም የህግ ማስከበር ተግባሩን በመደገፍና የደንብ መተላለፍ ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት የበፉኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments