ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለ ከተማ ያስገነባው የአቅ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለ ከተማ ያስገነባው የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ

ባለስልጣኑ በአራዳ ክፍለ ከተማ ያስገነባው የአቅመ ደካማ ቤት አጠናቆ ለባለቤቶቹ አስረከበ

            12/12/2018 ዓ.ም
           ** አዲስአበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የአራዳ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በስሩ የሚገኙ ወረዳዎችን በማስተባበር በክፍለ ከተማው ወረዳ 04 ለሚገኙ አቅመ ደካማ ነዋሪ  መኖሪያ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቱ አስረክቧል።

በምርቃቱ መርሐ ግቡሩ የተገኙት የአራዳ ክፍለ ከተማ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዲ ሙሉነህ ደንብ ማስከበር ለከተማው ህዝብ ደራሽ በመሆን የሀገሩን ልማት ለማስቀጠል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በትጋት እንደሚሰራ በመግለፅ ዛሬም በበጎ ተግባራ በክፍለ ከተማው ላስቀመጠው አሻራ  ምስጋና አቅርበዋል ።

በፕሮግራሙ የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ ሻምበል ኑርልኝ ገ/ኪዳን የክረምት በጓ ፈቃድ ስራዎች ከሆነው  ሰው ተኮር ተግባር የአቅመ ደካማ ቤት በመገንባት በ27 ቀናት  ሰርቶ በማጠናቀቅ  ለባለቤቷ ማስረከቡን ገልፀዋል ።

አክለውም  የአራዳ ክፍለ ከተማ  ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት  ባሉ 8 ወረዳዎች ከሚሰራቸው  የደንብ መተላለፍ መከላከልና መቆጣጠር በተጨማሪ ሰው ተኮር ስራዎች  አንዱ የስራው አካል አድርጎ እንደሚሰራ  በመጠቆም ለዚህም 1,454,200 ብር  በማውጣት የወ/ሮ ከበቡሽ ሸዋ ቤት አፈርሶ መገንባቱን ተናግረዋል ።

ቤቱ የተገነባላቸው ወ/ሮ ከበቡሽ ሸዋ ከ5 በላይ ቤተሰብ ይዘው የሚኖሩበት ቤት  ቀደም ሲል  ዝናብና ፀሀይ የሚፈራርቅበት  የነበረና ለመኖር  ፈታኝ እንደነበር በመግለፅ  ለተደረገላቸው ነገር ሁሉ ለደንብ ማስከበር ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አበርክተዋል።

በመድረኩ የተሳተፉት የአራዳ  ክፍለ ከተማ የበጓ ፈቃድና ህብረተሰብ ተሳትፎ ኃላፊ ወ/ሮ ፀጋነሽ ታምራት ደንብ ማስከበር በክፍለ ከተማው ከተለዮ የአቅመ  ደካማ ቤት አንዱ የሆነውን ቤት በአጭር ጊዜ አፍርሶ ከማደስ ባሻገር የተለያዩ ቁሳቁሶችን በማሟላት ለወገን ደረሽነቱን በማስመስከሩ  እጅግ የሚበረታታ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም ለበጓ አድራጎት ስራው ተሳታፊ ለነበሩ አካለት  የምስክር ወረቀት በመስጠት  ፕሮግራሙ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments