ባለስልጣኑ በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ ለዘርፎችና ለክፍለ ከተማ ፅ/ቤቶቹ ካስኬድ በማድረግ ተፈራረመ

ባለስልጣኑ በከተማው የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ ለዘርፎችና ለክፍለ ከተማ ፅ/ቤቶቹ ካስኬድ በማድረግ ተፈራረመ
   
             ነሐሴ 07/2018ዓ.ም
               **አዲስ አበባ** 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2019 በጀት ዓመት እቅዱ የደንብ መተላለፎች ለመቀነስ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ  ከዘርፎች እና ክፍለ ከተሞች ጋር የካስኬዲንግ እቅድ  መፈራረም መርሃ-ግብር  አካሄደ።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ሊያሰሩ የሚችሉ እቅዶችን በማቀድና በተሳካ ሁኔታ በማስፈጸም በከተማ ደረጃ ተሸላሚ መሆን መቻሉን ገልጸዋል። ለዚህ ስኬት የተቋም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መሰራታቸው፣ ለአመራሩና ለኦፊሰሮች የተሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንዲሁም ህብረተሰቡን ያሳተፉ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

​ሻለቃ ዘሪሁን በቀጣይም ስራዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በርካታ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል። በዚህም መሠረት የተያዙ እቅዶችን እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ በየጊዜው መገምገም እንደሚገባ፣ ህብረተሰቡ ስለ አዋጁ፣ ደንብና መመሪያዎች በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ የደንብ መተላለፎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚያስፈልግና ደንብ በሚተላለፉ አካላት ላይ ደግሞ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።

በተጨማሪም ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚደረጉ የቅንጅት ስራዎችን ማጠናከር፣ አሰራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ማዘመን፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻልና ብልሹ አሰራርን በመታገል ህብረተሰቡን በቀናነት ማገልገል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት በርካታ ዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ግቦችን ለማሳካት ማቀዱን የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ገልጸዋል።

ከተያዙት ግቦች መካከል የእጩ ፓራሚሊተሪ ኦፊሰሮችን ቁጥር በማሳደግ 2,380 አዲስ ምልምሎችን ማሰልጠን፣ ህግ በሚተላለፉ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድና የክትትል ስራዎችን በማጠናከር የደንብ መተላለፎችን (በ52%) መቀነስ ይጠቀሳሉ።

ከዚህ ጎን ለጎን በማህበረሰብ አደረጃጀቶች፣ በቤት ለቤት እና በቡና ጠጡ ውይይቶች የሚከናወኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ወደ 1.9 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ለማድረስ ታቅዷል።

​ተቋሙ በማህበራዊና በበጎ አድራጎት ዘርፍ 20,000 ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ  የአቅመ ደካማ ቤተሰቦችን ቤት በማደስ ላይ የሚገኝ መሆኑን እንዲሁም ማዕድ ማጋራት ለማከናወን አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ የተዘረጉትን አሰራሮችና የዲጂታላይዜሽን ስራዎች በውጤታማነት በመጠቀም አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ውብ እና ህግ የሚከበርባት ከተማ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑ ተገልጻል። 

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments