ባለስልጣኑ ለእጩ አመራሮች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ለእጩ አመራሮች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በስኬት በማጠናቀቅ እውቅናናና ምደባ ሰጠ

ባለስልጣኑ ለእጩ አመራሮች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና በስኬት በማጠናቀቅ እውቅናናና ምደባ ሰጠ

          ነሐሴ 04/2018ዓ.ም
          ****አዲስ አበባ**** 

​የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለተወጣጡ እጩ አመራሮች ላለፉት ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየውን የመሪነት እና የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠና በማጠናቀቅ እውቅና ለ7ሴት ሰልጣኞች እና ለ2 ወንድ በድምሩ ለ9 ሰልጣኞች ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊነት ምደባ መስጠቱ  ገለፀ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት ያመጣውን የአንደኝነት አፈጻጸም አጠናክሮ ለማስቀጠል፣ ከተማችን እያሳየች ያለችውን ፈጣን እድገት በሚመጥን መልኩ በእውቀት የሚመራ፣ በመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ጥብቅ እርምጃ የሚወስድ እና የህዝብን የአገልግሎት እርካታ የሚያረጋግጥ ብቁና ንቁ አመራር ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።

ስልጠናው  በቴክኖሎጂ የተደገፈ እና ወደፊት ለሚተገበረው እና አሁን ላይ ለሚያከናውኗቸው ተግባራትና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት ከፍተኛ አጋዥ መሆኑ ተገልጿል ።

ሰልጣኞችም በቆይታቸው ያገኙትን የላቀ እውቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የተቋሙን ዘላቂ እድገት ለማረጋገጥና የህዝብ አገልግሎትን ለማሻሻል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እጩ አመራሮች በስልጠና ማጠቃለያው ተቋሙ አሁን የደሰሰበት የቴክኖሎጂ የደንብ መተላለፎች የቁጥጥር ስርዓትና የተቋም ግንባታ ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments