የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የቢሮ ውስጥ እድሳቱን አጠናቆ አስመረቀ
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የቢሮ ውስጥ እድሳቱን አጠናቆ አስመረቀ
ሐምሌ 28/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤቱ የቢሮ ውስጥ እድሳት በማጠናቀቅ ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር አስመረቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በምርቃት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የተቋም ግንባታና አደረጃጀትን ማሻሻል ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ ለዜጎች ፍትሃዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።
በምርቃት መርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ ደንብ ማስከበር የደንብ መተላለፎችን በመቆጣጠር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት ከመፈጸምና በኃላፊነት ከመወጣት ባሻገር ያከናወነው ይህ የተቋም ግንባታ ስራ የሚበረታታና ሌሎች ጽህፈት ቤቶችንም የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።
ዘገባው ፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments