ባለስልጣኑ በላስቲክና ፌስታል ደንብ ቁጥር 13/...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በላስቲክና ፌስታል ደንብ ቁጥር 13/83/2017 ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በላስቲክና ፌስታል ደንብ ቁጥር 13/83/2017 ዙሪያ  የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ

        ሐምሌ/28/2018
       **የአዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ  ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በደንብ ቁጥር 13/83/2017 በፕላስቲክና ፌስታል ብክለት ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ  የደንብ ማስከበር  ጽ/ቤት ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ
ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንዳሉት ተቋሙ በከተማ አስተዳደሩ የሚወጡትን ደንቦች አስቀድሞ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የደንብ መተላለፉን የሚጸየፍ ማህበረሰብን ለመገንባት በተለያዩ መንገዶች ስልጠናዎችን የሚሰጥ መሆኑን ገልፀው፤ ሰልጥኖ ለማሰልጠን ዝግጁ እንዲሆኑ አሳስበዋል።

ከአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ ከአከባቢ ጥበቃ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሙላቱ ወሰኑ ስለ ፌስታል ብክለት መከላከልና የሚያስከትሉት ጉዳቶች ገልፀው ደንቡ በሚተገበርበት ወቅት ስለሚወሰደው እርጃ በስፋት አብራርተዋል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የሰልጥኖ አሰልጣኞችም የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ትምህርታዊ እውቀትን የቀሰሙበትና ወደ ታች በመውረድ ለማሰልጠን ተገቢውን እውቀት እንዳገኙ ገልጸዋል።

መረጃው፡- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments