ባለስልጣኑ ለደንብ ማስከበር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ለደንብ ማስከበር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈራረመ

ባለስልጣኑ ለደንብ ማስከበር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት ስምምነት ተፈራረመ

             ሐምሌ 28/2018ዓ.ም
             **አዲስ አበባ**    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከአዲስ አበባ ከተማ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ጋር ለፖራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የውል ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱ የደንብ ማስከበር አባላት የከተማዋን ፀጥታ እና ደንብ የማስከበር ስራ በሚያከናውኑበት ወቅት የሚገጥማቸውን የትራንስፖርት እንግልት በእጅጉ እንደሚቀርፍ ታምኖበት የውል ስምምነት መደረጉ የባለሥልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን እንደተናገሩት ኦፊሰሮቹ ይህንን የትራንስፖርት እድል ማግኘታቸው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን በማቃለል ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት እንዲኖራቸው የሚያደርግና ለከተማዋ ሰላምና ደንብ መከበር የሚሰጡትን አገልግሎት የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

​ይህ ውሳኔ ለአባላቱ የተደረገ ትልቅ እውቅና እና ድጋፍ ሲሆን በቀጣይም የከተማዋን ደንብና ስርዓት ለማስከበር ለሚደረገው ጥረት የሚደግፍ አሰራሮች እንደሚዘረጉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ  አቶ አካሉ አሰፋ በውል ስምምነቱ ለከተማችን ደንብ የሚያስከብሩ እና የመንገድ ደንነት በማስከበር መንገድ እንዳይዘጋጋ ጤናማ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የደንብ ማስከበር አባላት አገልግሎት ስንሰጥ ክብር ይሰማናል ብለዋል።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments