የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበ...

image description
- In code inforcement    0

የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ

የባለስልጣኑ አመራር እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ

      ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም
     **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች በአንድ ጀምበር 8 መቶ ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አሻራቸውን እያኖሩ ይገኛሉ።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ብቻ 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ግብ ለማሳካት በአንድ ላይ በመሰለፍ የታሪክ አካል እየሆኑ ይገኛሉ።

ዛሬ የምትተከለው እያንዳንዷ ችግኝ ለምግብ ዋስትና፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃ፣ ለምግብ አቅርቦትና ለቀጣይ ትውልድ ንጹህ አየር ዋስትና ናት።

ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፣ ነገ የምንሰበስበው አረንጓዴ ተስፋ ነው።

የትም ይሁኑ የት፣ በሚኖሩበትና በሚሠሩበት አካባቢ ቢያንስ አንድ ችግኝ በመትከል የዚህ ታሪካዊ ዕለት አካል ይሁኑ።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን!


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments