የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አአገልግሎት አሰጣጥ...

image description
- In code inforcement    0

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አአገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ስራ በወረዳ ፅ/ቤቶቹ መተግበር መጀመሩ ተገለፀ

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን አአገልግሎት አሰጣጥ የሪፎርም ስራ በወረዳ ፅ/ቤቶቹ መተግበር መጀመሩ ተገለፀ

       25/10/2018 ዓ.ም
     **አዲስ አበባ**   

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለሰራተኞች ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር ያከናወነውን የሪፎርም፣ የተቋም ግንባታ ስራዎች ከማዕከል አስከ ወረዳ የሚገኙ ኃላፊዎች በተገኙበት የቢሮ ጉብኝት ተካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እየተከናወነ የሚገኘው ምቹ የስራ አከባቢን የመፍጠር እና የሪፎርም ስራዎች የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት የሚያግዝ የሰራተኛውን የስራ ተነሳሽነት የሚጨምር እንዲሁም የምንሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ የሚጨምር መሆኑን ገልጸዋል ።

አክለውም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቅረፍ ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር  አአገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ማዘመንና ቀልጣፋ ማድረግ እንደሚገባና እየተከናወኑ የሚገኘው የሪፎርም ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።

ወረዳው በከተማ ደረጃ የተጀመረውን የሪፎርም ስራ በማስቀጠል ለሰራተኞች እና ለተገልጋዮች ምቹ የስራ አከባቢ በመፍጠር እንዲሁም ስራዎችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግና የደንብ መተላለፎችን በዘመናዊ መንገድ ለመከታተል ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ጋር በመተባበር የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል አዘጋጅቷል
በተጨማሪም ለሰራተኞቹ ምቹ የማደሪያ ክፍል፣ ልብስ መቀየሪያ ፣ ምግብ ማብሰያ ክፍልና ሻወር ቤት አዘጋጅቷል ።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች አሁን በወረዳው የታየው አበረታች አፈጻጸም በሚሰሩበት አካባቢዎች ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው በመሆኑ የተጀመረውን የሪፎርምና የተቋም ግንባታ ሥራ በላቀ ደረጃ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments