ባለስልጣኑ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ

ባለስልጣኑ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄደ

               23/10/2018 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን "ተስፋን እንትከል " በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ፍቃድ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርዓ ግብር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በብሔረ ጽጌ ፓርክ አካሂዷል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ  እንደገለጹት ይህ የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና በከተማችን ከንቲባ የተጀመረውን የ90 ቀን የክረምት እቅድ ለማስቀጠል ተቋሙ የጀመረው ስራ መሆኑን ጠቁመዋል።
አክለውም ባለስልጣኑ ባለፈው ዓመት 18 ሺህ ችግኞችን የተከለ ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት  ተጨማሪ 2 ሺህ  በመጨመር በአጠቃላይ 20 ሺህ ችግኞችን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እንደሚተክል አስታውቀዋል።

ተስፋን መትከል ማለት ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን ብሩህ አድርጎ ማየት ማለት ነው፤ ነገ ብሩህ የሆነ ብልጽግናን ማየት ማለት ነው። ዛሬ የተከልነውን ነገ ፍሬውን እንለቅማለን ሲሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

ከችግኝ ተከላው በተጨማሪም ተቋሙ የደም ልገሳ፣ የማዕድ ማጋራት እና ሌሎች የበጎ አድራጎት ስራዎችን በቀጣይ እንደሚያከናውን አረጋግጠዋል።

​የመርኃ ግብሩ የክብር እንግዳ የሆኑት የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ሀሰን  የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ስያሜውን ቀይሮ በህዝብ ዘንድ የነበረውን የእምነት ጉድለት በማረምና የሪፎርም ስራዎችን በብቃት በመተግበር ዛሬ ለደረሰበት የላቀ ደረጃ ላይ መብቃቱን ገልጸዋል።

ይህ መርኃ ግብር ልምላሜን፣ የከተማችንን አረንጓዴነት፣ የነዋሪዎቿን ምግብ እና ተስፋን የምንተክልበት በመሆኑ ሁላችንም እጅ ለእጅ ተያይዘን የበኩላችንን ኃላፊነት መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ አቶ አህመድ ገልጸዋል ።

ዘገባው፡- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments