በከተማው ላይ ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ...

image description
- In code inforcement    0

በከተማው ላይ ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ሰላምና ደህንነቱ የተጠበቀ ከተማ ማስፈን ተችሏል"ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ

"በከተማው ላይ ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ ያሳተፈ ስራ በመሰራቱ ሰላምና ደህንነቱ የተጠበቀ ከተማ ማስፈን ተችሏል"ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ  አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊ
       
         ሚያዝያ 29 /2018 ዓ.ም
          **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና መልካም አስተዳደር ክላስተር የ2018 በጀት  የ9ወራት ዕቅድ አፈጻጸሙን ገምግሟል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ በግምገማው መድረክ ላይ  እንዳሉት  በበጀት አመቱ ከከተማው ማህበረሰብ ጋር በቅንጅት በመሰራቱ በርካታ ውጤት ያለው ስራዎች እንደተሰሩ ጠቁመው አዲስ አበባ ከተማ ለዜጎቿ ደህንነት የጸጥታ አጠባበቅ የህግ የበላይነት ለማስፈን ክላስተር በመፍጠርና በቂ ዕቅድ አዘጋጅቶ በርካታ ከሰላምና ፀጥታ ፣ ከደንብ ማስከበር ፣ ከፍትህ ስርአት ፣ ከኢኮኖሚ አሻጥር ፣ ከትራፊክ ደህንነት እና መሰል ተግባራት ላይ  ውጤት ያለው ስራ መስራት ተችሏል ብለዋል።

የህግ የበላይነትን  ማስፈን በመቻሉ  አህጉራዊ አለማቀፍዊ ጉባኤዎች ትላልቅ ሁነቶች የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉና ከስጋት ነጻ የሆኑ ቅድመ የወንጀል መከላከል ትኩረት ያደረጉ ስራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ  እየተሻሻሉና ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ የጸጥታው መዋቅር  መላው ሰላም ወዳዱን ማህበረሰብ በማሳተፍ የወንጀል ምጣኔን  ቅነሳ መሰረት ያደረገ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ የህግ የበላይነት የሰፈነባት የጠላት ሀይሎች ሴራ የማክሸፍ አዋኪ ድርጊቶችን የመከላከያና የመቆጣጠር ስራዎችም መሰራታቸው አብራርተዋል ።

በከተማው ላይ ሰላምና ደህንነት እንዲቀጥል የከተማውን ነባራዊ ሁኔታ የተረዳ የሰላም ሰራዊት የማደራጀት ስምሪት በመስጠት ህገ ወጥ የደንብ ጥሰቶችን መከላከል ህብረተሰቡንም የሰላም ባለቤት በማድረግ ህገ ወጥነትንም የሚጸየፍ ማህበረሰብ በመገንባት ነዋሪው ተባባሪነቱን የጨመረበት ፣  የኮሪደር ልማቱ በህገ ወጦች እንዳይበላሹና ስርቆት እንዳይኖር በጋራ መስራት፣  የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጽሙ ግለሰቦች ወደ ህጋዊ የግብይት ስርዓት እንዲገቡ  የማስቻል ፣  የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች የመቆጣጠርና የመከላከያ ስራዎች መስራት ላይ የተሰሩ ስራዎችን ማስቀጠልና መወሰድ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች  ከክላስተሩ አባላት ተነስተው ውይይትም ተደርጓል።

በመጨረሻም አሁን ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደ ምክንያት በመጠቀም የነዳጅ ሁኔታን መነሻ በማድረግ ከህግ ስርአት ውጪ የሆኑትን ወደ ስርዓቱ እንዱገቡ የማድረግ ፣  በከተማው ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ ታማኝነት ግልጽነት ያለው ለህብረተሰቡ ግልጽ የሆነ አሰራር መዘርጋት ፣  በፍትህ ስርዓቱ መሰረት ወንጀልንና ወንጀሎተግባር በቀጣይ ትኩረት ተደርገው የሚሰሩ ዋና ዋና ነጥቦች እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በዘጠኝ ወራት ውስጥ የአዲስ አበባ አስተዳደር የህግ ማስከበርና የመልካም አስተዳደር ክላስተር ምን ምን ጉዳዩችን አከናወኑ የሚሉትን ሀሳቦች በዝርዝር ያብራሩት ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ ክላስተር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው

ሪፖርቱን መነሻ በማድረግ ከክላስተሩ ቋሚ ኮሚቴዎች ለተነሱት ሀሳብና አስተያየት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክላስተሩ ሰብሳቢ ምላሽና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰተዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments