የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የለውጥ ጉዞና የሪፎርም ስኬቶቹ
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የለውጥ ጉዞና የሪፎርም ስኬቶቹ
09/08/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ሪፎርም ከተደረገ በኋላ ባሉት 3 ዓመታት የተቀናጀ የሪፎርም ስራ በማከናወን የከተማውና የተቋም ገፅታ እየገነባ ይገኛል፡፡
ተቋሙ የደንብ መተላለፎችን ከመቆጣጠር ባለፈ የውስጥ አሰራሩን በማዘመን እና ለሰራተኞቹም ሆነ ለተገልጋዮች ምቹ የስራ ሁኔታን በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግቧል፡፡
በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የተገነቡት የኮል ሴንተር እና የስማርት ስልጠና ማዕከላት ተቋሙን አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ ለመስጠት ምቹ ሁኔታ አየፈጠሩ ይገኛል።
ባለስልጣኑ ለህዝብ ግንኙነትና ለሚዲያ ስራዎች ተብሎ የተገነባው የድምፅና ምስል ስቱዲዮ ደግሞ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራው ለህብረተሰቡ በስፋት እንዲደርስ እያገዘ ይገኛል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለሰራተኞች ምቹ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር የተገነቡት ዘመናዊ የህጻናት ማቆያ፣ ጥራቱን የጠበቀ ካፌቴሪያ እና ጂምናዚየም ተቋሙ ለሰው ኃይል የሰጠውን ትኩረት የሚያሳዩ ማሳያዎች ናቸው፡፡
እነዚህ የሪፎርም ስራዎች በውጤት ታጅበው በ2018 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ብቻ በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በ82% መቀነስ ተችሏል፡፡
ባለስልጣኑ የተጀመረ የለውጥ ጉዞ እስከ ታችኛው መዋቅር ለማውረድ እና የበለጠ ለማጠናከር የክፍለ ከተማና የወረዳ የደንብ ማስከበር አመራሮች በዋናው መሥሪያ ቤት ጉብኝት በማድረግ ለሰራተኞቻቸውና ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጥሩ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments