"በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ለአመራሩ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም የሚገነባ ነው" አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ
"በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ እየተሰጠ ያለው ስልጠና ለአመራሩ የማስፈፀምና የመፈፀም አቅም የሚገነባ ነው" አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ
መጋቢት 20/2018 ዓ ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ለስትራቲጂክ አመራሮች እየተሰጠ ያለው ስልጠና በጥብቅ ዲሲፕሊን በእቅዱ እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ።
የስልጠናው አስተባባሪና የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ባደረጉት ገለጻ ስልጠናው በጥብቅ ዲሲፕሊን፤ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄደ እንደሆነ እና ለአመራሩ የማስፈፀምና የማስፈፀም አቅም የሚገነባ መሆኑ ተናግረዋል።
የኢትዩጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ የአመራርና አቅም ግንባታ ማእከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው ለአመራሮቹ እየተሰጠ ያለው ስልጠና በከተማው የደንብ መተላለፍን በመቀነስ የከተማዋን እድገት የሚመጥን አመራርነት አገልግሎት ለመስጠት ያለመ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ገልጸዋል።
ስልጠናው ወቅቱን መሠረት ያደረጉና ለቀጣይ ስራ አስፈላጊ የሆኑት በስትራቴጂክ መሪነት ፣ በብሔራዊ ስትራቴጂና ጂኦ ፖለቲካ፣ በእቅድና ሪፖርት ዝግጅት፣በህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ እና በጂዮ ስፓሻል ቴክኖሎጂ እርዕሶች ላይ ውጤታማ ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው በየአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ወታደራዊ ስልትን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ብቃት ስልጠናዎች ተሰጥተዋል።
መረጃው:- የባለ ስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments