የመሪነት ጥበብ የተላበሰ እና በአካል ብቃት የዳበረ አመራር ለውጤታማ ደንብ ማስከበር ተልዕኮ
የመሪነት ጥበብ የተላበሰ እና በአካል ብቃት የዳበረ አመራር ለውጤታማ ደንብ ማስከበር ተልዕኮ
መጋቢት 16 2018 ዓ ም
** ሰንዳፋ**
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አመራሮች "የመሪነት ጥበብ የተላበሰ እና በአካል ብቃት የዳበረ አመራር ለውጤታማ ደንብ ማስከበር ተልዕኮ " በሚል መሪ ቃል የስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ተካሄደ።
ውድድሩ አመራሩ በየትኛውም ጊዜ የሚሰጠው ተልዕኮ በመተባበርና እንዲወጣ አብሮነቱን ለማጠናከር እና የተሻለ ተግባቦት ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
በመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ረዳት ኮምሽነር ዳኒኤል ብረሀኑ ፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው፣ የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ፣ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው የኢትዩጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ የአመራርና አቅም ግንባታ ማእከል መምሪያ ኃላፊ በመገኘት ስፖርታዊ ውድድሩን አስጀምረዋል።
በዛሬው የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ከአራዳ ክፍለከተማ ግጥሚያ ያደረጉ ሲሆን በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ 4 አቻ በመጠናቀቁ በመለያ ምት ለሚኩራ ክፍለከተማ በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋን ሲያረጋግጥ በተመሣሣይ ልደታ ክፍለ ከተማን ከአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ያገናኘው ጨዋታ በመደበኛው የጨዋታ ጊዜ 1 አቻ በመጠናቀቁ በመለያ ምት ልደታ ክፍለ ከተማ አሸንፎ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፋን አረጋግጧል።
በእለቱ የባለስልጣኑ የሴት አመራሮች መካከል አዝናኝ የእግር ኳስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን የተቋሙ ሴት አመራሮች በአመራርነት ጥበብ በተጨማሪ አስደና ቂ የአካል ብቃት አሳይተዋል።
ውድድሩ እንደቀጠለ ሲሆን በነገው እለትም የተለያዩ የጨዋታ መርሀ ግብሮች እንደሚደረጉ ከውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ተመላክቷል።
መረጃው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments