ችግኞችን እንደ ህፃን እንክብካቤ ይሻሉ እንዲፀድቁ በዘላቂነት እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል
ችግኞችን እንደ ህፃን እንክብካቤ ይሻሉ እንዲፀድቁ በዘላቂነት እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል
07/07/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 ዓ.ም የተቋም ምቹ አከባቢ ለመፍጠርና የተተከሉ ዕፅዋት በዘላቂነት እንዲጸድቁና ተገቢው እንክብካቤ እንዲደረግላቸው የሚያስችል የተቀናጀ የማስፈጸሚያ ዕቅድ ውይይት አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር የተቋም ምቹ የስራ አካባቢ ለመፍጠር የተተከሉ ዕፅዋት እንዲጸድቁ ለማድረግ የተዘጋጀ የማስፈጸሚያ ሰነድ ገለፃ ተደርጓል።
የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር እያንዳንዱ የተተከለ ችግኝ ግልጽ የሆነ ተንከባካቢ ወይም ባለቤት እንዲኖረው በማድረግ ችግኞች ሳይደርቁ እንዲጸድቁ ማስቻል እንደሚገባ አቶ ስንታየሁ ተናግረዋል ።
የተቋም ምቹ የስራ አከባቢን ለመፍጠር ችግኞች በባለቤትነት እንክብካቤ ለማድረግና ለማሳደግ የተቋሙ አመራሮች ለዳይሬክተሮች እንዲሁም ዳይሬክተሮች ለባለሙያዎች ችግኞችን ርክክብ ተደርጓል ።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments