ባለስልጣኑ ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
ባለስልጣኑ ከግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ጋር የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የቅንጅታዊ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ
26/06/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ባለስልጣን "ህገወጥነትን -በቅንጅት "በሚል መሪ ቃል ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ የ2018 በጀት የግማሽ ዓመት በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት የታቀዱ ተግባራት ክንውንን በመገምገም፣ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠልና ድክመቶችን ደግሞ በማረም በተቋማቱ ያለውን ቅንጅት ማጠናከር በቀጣይ በጋራ የምናከናውናቸውን ተግባራት በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም ውይይት መደረኩ እንደሚያግዝ ገልፀዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት የተቋም ግንባታ ስራን በማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በማስጀመር ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት በመስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ህገወጥ ግንባታ እና ህገወጥ ማስታወቂያ እና ሌሎች የደንብ መተላለፎችን የሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል ፡፡
በመድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ህይወት ሳሙኤል በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን የሥራ ግንኙነት በማጠናከር፣ ሕገ-ወጥ ግንባታን በጋራ መከላከልና የከተማዋን ስማርት ሲቲ ግንባታ ማፋጠን የውይይቱ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም ሕገ-ወጥ ግንባታዎችንና ህገወጥ ማስታወቂያዎችን በመለየትና አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ ረገድ የታየው ቅንጅት ስራ ውጤታማ በመሆኑ በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ከደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጋር የ2018 ዓ.ም የግማሽ ዓመት አፈጻጸም የውይይት ሰነድ የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ኢንጅነር አበበ እሸቱ ቀርቧል ።
ህገወጥ ግንባታ እና ህገወጥ ማስታወቂያ መከላከል ስራ ጎን ለጎን በጥፋት ከተገኙ አካላት ከ106 ሚሊዮን ብር በላይ በላይ ገቢ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉን በሰነዱ ተገልጿል ።
በቀሪዎቹ ስድስት ወራት ሕገ-ወጥ ግንባታዎችንና የውጪ ማስታወቂያዎችን በዘላቂነት መከላከል፣የግንባታ ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ክትትል ይበልጥ ማጠናከር ፣ የግንባታ ተረፈ ምርቶችንና ቁሶችን መንገድ ላይ የሚያስቀምጡ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ እንዲሁም በሁለቱም ተቋማት በኩል የሚታዩ የሥነ-ምግባር ችግሮችን ለመቅረፍ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን አጠናክሮ መቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል ።
በመድረኩ ላይ በግማሽ ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
በውይይት መድረኩ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች የደንብ ማስከበር የማዕከል ዳይሬክተሮች እና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments