ባለስልጣኑ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ ለክፍለ ከተማና ለወረዳ የኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ
5/6/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለክፍለ ከተማ እና ለወረዳ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤ የኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች /focal person/ በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ለይ ግንዛቤ በመፍጠር የዳይሬክቶሬቱ የ6 ወራት የስራ ክንውን ላይ ውይይት አካሂዷል ።
መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ኮሙኒኬሽን ለተቋም ግንባታ ስራዎች ተደራሽ ለማድረግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ የሚሰጠውን ስልጠና ተግባራዊ በማድረግ የባለስልጣኑን ደንቦች መመሪያዎች አዋጆች ለከተማው ህዝብ ግንዛቤ በመፍጠር የባለስልጣኑ መረጃዎች መሸጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
አያይዘውም ለኮሙኒኬሽን ተወካዮች ስልጠና በመስጠት የጋራ ውይይት በማድረግ የመረጃ ልውውጥን በማዘመን የተቋሙን ገጽታ መገንባት የሚያስችል ስራዎች ለመስራት የኮሙኒኬሽን ስራ መጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈፃፀም የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ የቀረበ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም፣ የሚያስከትለው ጉዳት እና የሚዲያ ሞኒተሪንግ ምንነት እና አስፈላጊነት የተመለከተ ሰነድ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ወ/ሮ ኤደን በዳሶ አማካኝነት በዝርዝር ቀርቧል ።
በተጨማሪም የየካ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ተወካይ አቶ ዘላለም ፈቃደ አገልግሎት አሰጣጥ ሽግግርና ደንበኞች ግንኙነት አስፈላጊነት ፣ የሚጠበቅ ውጤትና ስኬትና የወደፊት አቅጣጫ የሚያሳይ ሰነድ አቀርቧል።
በመድረኩ ከኢዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የደንብ አዲስ አዘጋጅ የሆኑት አቶ ፈቃዱ ምስጋናው የባለስልጣኑ የፓራ ሚሊታሪ ኦፊሰሮች ለከተማው እድገትና ለውጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልፀው ይህንንም በሚዲያ ለማዋል የህዝብ ግኑኝነት ስራዎች ተጠናክሮ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
ተሳተፊዎቹ የተሰጠው ስልጠና ለኮሙዩኒኬሽን ተወካዮች የሚያግዝና የሚያነቃቃ መሆኑን በመጠቆም ፣ በወረዳና በክፍለ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ መደብ ቢኖር እና ለተወካዮች የግብዓት አቅርቦት ቢሟላ የሚሉ ጥያቄዎች አንስተዋል።
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃለፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ እና በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ የምሰራች ግርማ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት መድረኩ ተጠናቋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments