የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ከማዕከ እስከ ወረዳ የአመራሩና ሰራተኞች አንድነትና ቅንጅት ያስደንቃል"የሀረሬ ከተማ የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን አባላት
"የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ከማዕከ እስከ ወረዳ የአመራሩና ሰራተኞች አንድነትና ቅንጅት ያስደንቃል"የሀረሬ ከተማ የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን አባላት
04/06/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የቂርቆስ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከሀረር ከተማ ለመጡ ልዑካን ቡድኖች በክፍለ ከተማው ስላለው አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ ልምድና ተሞክሮዎችን አካፈለ።
የሀረር ከተማ የመጡ ልዑካን ቡድኖች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመገኘት በክ/ከተማው ስለ ሚከናወኑ የደንብ መተላለፍ የመከላከል የመቆጣጠርና እርምጃ የመውሰድ ስራዎች ፣ ለህብረተሰቡ ስለሚሰጥ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች ፣ የፖራ ሚሊተሪ የስምሪት አሰጣጥ ፣ አደረጃጀትና የስራ እንቅስቃሴዎች ጉብኝትና ምልከታ አድርገዋል ።
የቂርቆስ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ ተክሉ በተሞክሮ ማጋራቱ ወቅት እንተገለጹት ደንብ ማስከበር የተቋም ግንባታ ስራዎችን በማጠናከርና 7/24 የስራ ባህል አድርጎ ቀን ከለሊት ሳይል በርካታ ስራዎች በማከናወን እንዲሁም ስራዎችን በቅንጅት መስራት በመቻሉ በክፍለ ከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰትን ለመቀነስ ማስቻሉን ገልጸዋል ።
የሀረር ከተማ የልምድ ልውውጥ የልዑካን ቡድን አባላት የከተማው ደንብ ማስከበር ከማዕከ እስከ ወረዳ አመራሩና ሰራተኞች በተቋሙ አሰራር ላይ ያለልዩነት ተመሳሳይ ቋንቋ ተነሳሽነትና የለውጥ አላማ መደነቃቸው ገልፀው ያገኙት ልምድና ተሞክሮ በክልላቸው ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ተናግረዋል ።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments