ባለስልጣኑ ከሀረሬ ክልል ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ
ባለስልጣኑ ከሀረሬ ክልል ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት የስራ ልምዱና ተሞክሮውን አጋራ
04/6/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከሀረሬ ክልል ለመጡ የልዑካን ቡድን አባላት ስለ ባለስልጣኑ አጠቃላይ አደረጃጀት፣ የስራ እንቅስቃሴዎችንና አሁን ላይ የደረሰበት ለመድረስ የተሄደበትን መንገድ የተመለከተ ልምድና ተሞክሮ አጋራ።
የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ልምድ ለመቅሰም ለመጣው ልኡካን ቡድን የባለስልጣኑን አጠቃላይ መዋቅር እና አሁን ለይ የተደረሰበት አቋም ለመድረስ የተሄድበትን መንገዶች ገለፃ አድርገዋል ።
ባለስልጣኑ አሁን ላይ ከ8 ሺህ በላይ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች እንዳሉት እና በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ ጥሰቶችን የመከላከል የመቆጣጠር እና እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ በከተማ አሰተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን የመጠበቅ እና አዳዲስ የሚወጡ የከተማዋን ህጓች የማስፈፀም ስራ እንደሚሰራ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
በልምድ ማጋራቱ ወቅት በምክትል ስራ አስኪያጅ ማዕረግ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ሀላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና የክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው ታደሰ ስለ ፓራሚሊተሪ አፊሰርሮች ስልጠና አሰጣጥ ፣ ለከተማው ህዝብ ግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች የሚደረግባቸው መንገዶችና በደንብ ጥሰቶች ዙርያ በሚደረግ ቁጥጥርና አርምጃ አወሳሰድ ሂደት አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።
የሀረሬ ክልል የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብሳ አልይ ልምምድ ልውውጥ ማድረጉ የተሻሉ አሰራሮችን ተሞክሮዎችን በመውሰድ ለክልሉ ወስዶ በመተግበር ውጤት ለማምጣት የሚያግዝ መሆኑን በመግለፅ ህገወጥ ግንባታ ለመከላከልና ለመቆጣጣር የተሄደበት መንገድ የፓራ ሚሊተሪ እና የሲቪል ሰርቫንቱን የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ ላይ የሚሰራበት መንገድ እንዲብራራላቸው ጠይቀዋል ።
ለልምድ ልውውጥ ለመጡ አካላት "ደንብ ማስከበር ከየት ወዴት" በሚል የተዘጋጀው ሰነድ በባለስልጣኑ የስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት እና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ቀፀላ ቀርቧል።
በሰነዱ ሰለ ባለስልጣኑ ምስረታ፣ አዋጆች ደንቦች መመረያዎች፣ በተቋም አደረጃጀት ፣ በአሰራር፣ በመመሪያ ዝግጅት ፤በሰው ሃይል አደረጃጀት፣ ስለ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር የስልጠና ሄደት ፣ በከተማዋ የለሙ የመሰረተ ልማት ስለ መጠበቅ ፣ የተቋሞ ግንባታ ስራዋች እና ዘመናዊ ቴክኖሎጅ ከመተግበር አንፃር የተሰሩበት ያለ ስራዎችን በተመለከተ ባለስልጣኑ ያለውን ልምድና ተሞክሮ በዝርዝር አቀርቧል፡፡
ልዑካን ቡደኑ የባለስልጣኑን አጠቃላይ የቢሮ አደረጃጀትና በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በመዘዋወር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስምሪትና የመስክ የስራ ክንውን ጉብኝት በማድረግ ልምድ ልውውጥ ተጠናቋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments