ለአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ የደንብ ማስከበር ሚና...

image description
- In code inforcement    0

ለአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ የደንብ ማስከበር ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

ለአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ የደንብ ማስከበር ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ

            የካቲት  3/2018 ዓ.ም
         **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና  በ11 ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ከ119 ወረዳ ከመጡ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን ግምገማ አካሄደ ።

መድረኩ በሀገር ሽማግሌና በሐይማኖት አባቶች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን የባለሥልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ባለስልጣኑ የከተማዋን ደንብ ጥሰቶች በመከላከል በመቆጣጠር በከተማዋ የሚሰሩ ልማቶችን ውበታቸው ተጠብቆ እንዲቆዩ  ማድረግ መቻሉ ገልፀዋል ።

የጽ/ቤት ኃላፊው አክለውም ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት የደንብ መተላለፎችን በ87 ፐርሰንት መቀነስ  መቻሉ ገልጸዋል ።

በደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2018 በጀት አመት የ6ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የባለስልጣኑ የእቅድና በጀት  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮ/ል አድማሱ ተክሌ  ቀርቧል።

በሪፖርቱ ባለፉት ስድስት ወራት በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን፣  የተቋም  ግንባታ ስራዎች መሰራታቸው ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት መሰጠት መቻለቸው ፣የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ስራዎች መሰራታቸውና የደንብ ጥሰቶችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዋች መሰራቱ በሪፖርቱ ቀርቧል ፡፡

በመድረኩ የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ባለስልጣኑ የደንብ መተላለፎችን ለመቀነስ ከህብረተሰብ ጋር በጋራ መሰራት በመቻሉ እና በየጊዜው ውይይት ምክክር በማድረጉና በቅንጅት በመስራቱ ከፍተኛ ለወጥ ማምጣት መቻሉን ገልፀዋል ።

ከመድረኩ ተሳታፊ የህብረተሰብ ክፍሎች ለአዲስ አበባ ከተማ ለውጥ የደንብ ማስከበር ሚና ከፍተኛ መሆኑን፣ከፓሊስ ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ይበል እንደሚያሰኝ፣ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ በሶስት ሽፍት መደረጉ ያለወን ጠቀሜታና የመጠለያ ችግራቸው መቀረፍ ቢቻል የሚሉ ሀሳቦች ተነስተዋል ።

በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳብና አስተያየት  ሰፊ ውይይት በማድረግ ለተነሱ ሀሳብና ጥያቄዎች በተቋሙ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።

ዘገበው ፡- ባለሥልጣኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments