ባለስልጣኑ በኢትዮጲያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ በተከታታይ በስምንት ዙር ለነባር ኦፊሰሮቹ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ
ባለስልጣኑ በኢትዮጲያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ በተከታታይ በስምንት ዙር ለነባር ኦፊሰሮቹ ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና ማጠናቀቁን አስታወቀ
03/06/2018 ዓ.ም
ሰንዳፋ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ዙር ሲሰጥ የቆየውን የወታደራዊና የስነ ምግባር ስልጠና በማጠናቀቅ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ ውይይት የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋማችን በየጊዜው ራሱን የማዘመንና የማጠናከር ስራ የሚሰራው ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ በመሆኗ የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ሰላምና ጸጥቷ የተጠበቀ ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ ጽዱ ማራኪ በማድረግ በስነምግባር የታነጸ ኦፊሰር በመገንባት የተሰጠንን ተልዕኮ በውጤት ለመወጣት ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል ።
አቅማችንን በየጊዜው በማሻሻል እንዲሁም በቴክኖሎጂ በመደገፍ እና ከባለድርሻና ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር በመስራት በከተማዋ ውስጥ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን በመከላከል የከተማዋን ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየት የህብረተሰቡን ደህንነት የማስጠበቅ ከፍተኛ ስራ በደንብ ማስከበር መሰራቱንና በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
አክለውም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በማበመን ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ የሙያዊ ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የከተማችን ፈጣን እድገት ያማከለ ወቅቱን የሚመጥን ስልጠናዎችን ለአመራሩና ኦፊሰሮች በመስጠት ተቋሙ በከተማው አስተዳደር የተሰጠውን ተልዕኮ በውጤት በመፈጸም የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በዛሬው ዕለትም ከ8000 በላይ ኦፊሰሮች በኢትዮጲያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ በ8 ዙሮች ሲሰጥ ቆይቶ ማጠናቀቁን ተናግረዋል።
በቀጣይም አመራርና ኦፊሰሩን ለማብቃት በየጊዜው ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎች እየተዘጋጁ የሚሰጥ መሆኑን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ተናግረዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments