ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ግ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ
              
                02/06/2018 ዓ.ም
                   **ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ8ኛ ዙር ነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች  የከተማዋን እድገት የሚመጥን ፣ ዘመናዊነትን የተላበሰ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል  ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና  በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል።

የተቋሙ  የስነ -ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ የስልጠናዉን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን  ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የስራ ስነ-ምግባር በመላበስ ሙያዊ ሀላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣና ወቅቱ የሚፈልገውን አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል  አቅሙን ለማሳደግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌላኛው ተመሳሳይ የስልጠና ሰነድ ያቀረቡት የባለስልጣኑ የክትትል ቁጥጥር እና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል የደንብ ማስከበር ስራዎችን ስናከናውን ሙያዊ ስነ ምግባርን ካልተላበስን አገልግሎት አሰጣጥን ውጤታማ ማድረግ አይቻልም በማለት ሰልጣኝ ኦፊሰሮች ሙያዊ ስነ ምግባር ላይ ልዩ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በግምገማዊ ስልጠናው ላይ ተልዕኮን ከአመራር ተቀብሎ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ፣ ከሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች ፣ ከህግ እንዲሁም ደንብና መመሪያ ተፈጻሚነት ጋር በተያያዘ ፣ ከሰብአዊ መብት አያያዝ አንጻር ስላሉ ክፍተቶች ፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አኳያ ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በዕለቱ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር132/2014 ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ቁጥጥር ፍተሻና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መማሪያ ጥቁር 163/2017 እና የአተገባበር ማንዋል ላይ የተቋማት የአደጋ ደህንነት ማካተትና  ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዘላለም አንለይ ስልጠና ተሰጥቷል ።

ከሰልጣኙ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኝ  ኦፊሰሮች በስልጠናው ራሳቸውን የተመለከቱበትና   ህብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ የሚያደርግ እውቀቶችን የቀሰሙበት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች ዙሪያ  የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና ሰብአዊ መብትን ከማስጠበቅ አንጻር ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ አቅጣጫ በማስቀመጥ ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments