በባለስልጣኑ እየተሰጠ ያለውን የነባር ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የፕላን እና ልማት ቢሮ የኢንስፔክሽን ቡድን ጉብኝት አካሂዱ
በባለስልጣኑ እየተሰጠ ያለውን የነባር ኦፊሰሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና የፕላን እና ልማት ቢሮ የኢንስፔክሽን ቡድን ጉብኝት አካሂዱ
29/05/2018ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በኢትዮጲያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ እየተሰጠ ያለውን የፓራ ሚሊተሪ የንድፈ ሀሳብና የአካል ብቃት ስልጠና ከፕላን እና ልማት ቢሮ የኢንስፔክሽን ቡድን የስልጠና አሰጣጥ ሂደቱን በዛሬው ዕለት ሰንዳፍ በሚገኘው ፓሊስ ዩኒቨርስቲ የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት የአካል ምልከታ አካሄደ።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው እንዳሉት በባለፈው የ6ወራት አፈፃፀም በቢሮ ውስጥ ኢንስፔክሽን የተደረገ መሆኑን አስታውሰው በዛሬው ዕለትም ባለስልጣኑ በተለያዮ ዙሮች እየሰጠ የሚገኘው ስልጠና አሁን 8ኛ ዙር ላይ መድረሱን ተናግረዋል ።
ምክትል ስራ አስኪያጁ አክለውም በቅድሚያ ይህ ስልጠና የፓራ ሚሊተሪውን የአካል ብቃት እና የስነ ልቧና አቅምን ከፍ እንዲያደርግ እንዲሁም ከተማዋን የሚመጥን ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ታስቦ የሚሰጡ ርዕሶች በጥናት ተለይተው የቀረቡ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የኢንስፔክሽን ቡድኑም ሰልጣኝ ፖራሚሊተሪ ኦፊሰሮች ፣ የዮንቨርስቲው የስልጠና ክፍል ኃላፊ እና የወታደራዊ ስልጠና ክፍል አስተባባሪ ጋር ቆይታ በማድረግ የስልጠና ሂደቱን ተከታትለዋል።
ዘገባው:- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments