ከውጭ ሀገራት እርዳታ እና ልመናን በማስቀረት ተ...

image description
- In code inforcement    0

ከውጭ ሀገራት እርዳታ እና ልመናን በማስቀረት ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋ የማይበገሩ ከተማና ሀገር ለመገንባት የዜጎች የነቃ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ

ከውጭ ሀገራት እርዳታ እና ልመናን በማስቀረት ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋ የማይበገሩ ከተማና ሀገር ለመገንባት የዜጎች የነቃ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑ ተገለፀ

                  25/05/2018 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ከተቋሙ ውጪ የሆነ እንግዳ በመጋበዝ የባለስልጣኑ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት አካሄደ፡፡

የመድረኩ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋሁን አሉላ ተረጂነትን እና ልመናን በመጠየፍ፣ ለማንኛውም ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋ የማይበገሩ ከተማና ሀገር መገንባት የሚቻለው በራስ አቅም ለመቆም በመተባበር እና አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል  መሆኑን ተናግረዋል ።

የዕለቱ የወርቃማ ሰኞ እንግዳ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የድህረ አደጋ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላከ ሠማኝ የድህረ አደጋ ዳይሬክተር  የሰብዓዊ ድጋፍ ሉአላዊነት በራሰ አቅም ማረጋገጥ እሳቤዎችና ማስፈንጠራያዎች" የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰነድ አቅርበዋል ።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ጽንሰ ሃሳብ በራስ አቅም ሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት ማሟላትን፣ሃገራዊ መሪነት አካባቢያዊ ባለቤትነትና አይበገሬነት በዘላቂነት ማረጋገጥ ብሎም የውጭ አካላት ጠባቂነትንና የእርዳታ ጥገኝነትን ማስወገድ የሚጠይቅ  መሆኑ ተገልጿል ።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት ጽንሰ-ሃሳብ ከምግብ ዋስትና በዘለለ የሀገርን ክብርና ነፃነት የማስጠበቅ ጉዳይ መሆኑን አቶ መላከ ተናግረዋል ።

​ተፈጥሮና ዘመን የለገሰንን ዕድል በፈጠራ እና በፍጥነት በመጠቀም፣ የውጭ አካላት ጠባቂነትን በማክሰም የሀገራችንን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በፅኑ መሰረት ላይ ማቆም እንደሚገባና ሁለንተናዊ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በጋራ መነሳት እንደሚገባ ተገልጿል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments