"ለባለስልጣኑ የተሰጠው እውቅናና ሽልማት ተቋሙ ለከተማዋ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው።" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
"ለባለስልጣኑ የተሰጠው እውቅናና ሽልማት ተቋሙ ለከተማዋ እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው።" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ
25/05/2018 ዓ.ም
** አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው የ60 ሚሊዮን ብር ዲጂታል የሎተሪ እጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት የእድለኞች የሽልማት ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ ለደንብ ማስከበር የተሰጠውን 2,500,000/ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ/ ብር የሽልማት ርክክብ አካሄደ ።
በሽልማት ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የተቀበሉትን የ2.5 ሚሊዮን ብር የሽልማት ቼክ መላው የባለስልጣኑ ሰራተኞች በተገኙበት ለዋና ስራ አስኪያጁ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ አስረክበዋል።
ባለስልጣኑ እውቅና የተሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፎችና ህገ-ወጥ ተግባራት በመከታተልና በመቆጣጠር እንደዚሁም በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማቶች ጥበቃ እያበረከተ ላለው የላቀ አፈጻጸም መሆኑ ተገልጿል ።
ስጦታውን የተረከቡት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የተሰጠው እውቅናና ሽልማት ተቋሙ ለከተማዋ ውበትና ስርአት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ በሚገባ የተረዳ መሆኑን ገልጸው፣ ለተደረገው እውቅና በባለስልጣኑ ስም ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም ይህ የተበረከተው የገንዘብ ስጦታ ተቋሙ በከተማዋ ለሚያከናውናቸው ሰው ተኮር የበጎ አድራጎት ተግባራት እንዲውል መታቀዱን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ሽልማት በቀጣይም ባለስልጣኑ የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የደንብ ማስከበር ስራዎችን ይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ትልቅ ሞራል እንደሚሆን ገልጸዋል ።
መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments