የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር...

image description
- In code inforcement    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ገቡ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ነባር  የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ገቡ 

            23/05/2018 ዓ.ም
              ** ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ነባር  የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ገቡ ::

ሰልጣኞቹ ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ459 በላይ የሚሆኑ የስምንተኛ ዙር ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ በባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች እና በፓሊስ ዩንቨርስቲው ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

በስልጠና መክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመውሰድ  ራሳቸውን ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ስልጠናው በሀገር ወዳድነት፣ በግጭት አፈታት ፣በመረጃ አያያዝ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በተግባቦት ክህሎት ፣ የእሳት አደጋን በመከላከል እና የአካል ብቃት ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ተመልክቷል ።

በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአመራርና አቅም ግንባታ ስልጠና ማዕከል መምሪያ ሃላፊኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩንቨርስቲው ከባለስልጣኑ ጋር በመተባበር የሚሰጠውን ስልጠና የዩንቨርስቲውን ህግና ደንብ በማክበር  ስልጠናው በትኩረት መውሰድ  እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት  እንደሚሰጥ  በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት አስላልፈዋል ።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments