ባለስልጣኑ የሚሰጠው አገልግሎትና ሰብአዊ እና...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ የሚሰጠው አገልግሎትና ሰብአዊ እና ማህበራዊ ድጋፍ እውቅናና ሽልማት ተሰጠው

ባለስልጣኑ የሚሰጠው አገልግሎትና  ሰብአዊ እና ማህበራዊ ድጋፍ እውቅናና ሽልማት ተሰጠው

             22/05/2018 ዓ.ም
            አዲስ አበባ     

በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው የ60 ሚሊዮን ብር ዲጂታል የሎተሪ እጣ አወጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለከተማችን ነዋሪዎች እየሰጠ ላለው ሰባዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በወጣው የ60 ሚሊዮን ብር ዲጂታል ሎተሪ እድለኞች የሽልማት  ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ እውቅና ተሰጠው።

በመድረኩ የክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው  በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው  የባለስልጣኑ 2,500,000/ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ/ ብር ሽልማቱ  ተረክበዋል፡፡

ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸውነ በንግግራቸው  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ለከተማው ያበረከተው አስተዋፅኦ በመረዳት እውቅናና ሽልማት በመሰጠቱ በከተማ አስተዳደሩና በባለስልጣኑ ስም  ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

ባለስልጣኑ እውቅና የተሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተላለፎችና ህገ-ወጥ ተግባራት በመከታተልና በመቆጣጠር እንደዚሁም በኮሪደር ልማትና በወንዝ ዳርቻ ልማቶች ጥበቃ  እያበረከተ ላለው የላቀ አስተዋፅዖ መሆኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሎተሪ አገልግሎት  እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ድርጅት ሀላፊዎች ገልፀዋል።

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደርና ታሚኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን የ60 ሚሊየን ብር ሽልማቱ በቀጣይ የዲጂታል ሎተሪን በማስፋፋትና ተደራሽነቱን በማሻሻል ሽልማቱ ከፍ ለማድረግ ሰራዎች መጀመራቸው አስታውቋል።

በእለቱ የባለስልጣኑ አመራሮችና ኦፊሰሮች ከሌሎች አመራሮችና የክብር እንግዶች ጋር በመሆን የሎተሪ አሸናፊዎች ሸልማቶቻቸው አበርክተውላቸዋል።

መረጃው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments