ስልጠና ተግባራዊ መሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
"ስልጠና አንዱ የተቋም ግንባታ መሳሪያ በመሆኑ የተሰጠው ስልጠና ተግባራዊ መሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል" ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ
22/05/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሰባተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካል ብቃትናና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሰንዳፋ በሚገኘው በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲ የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጲያ ፣ከተማችን አዲስ አበባ እና ተቋማቸውን የደረሱበት ደረጃ ገለፃ በማድረግ የተቋሙ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር በከተማችን ውስጥ ለለሙ መሰረተ ልማቶች ሰፊ አስተዋፅኦ እንዳበረከ ገልፀዋል።
ከተማ አስተዳደሩ በተቋሙ ከፍተኛ እምነት ስላለው የተለያዩ ደንብና መመሪያዎች እንዲያስተገብር ተልዕኮ ለመስጠትና ለመቀበል በእውቀት ላይ ተመስርቶ በቴክኖሎጅ ዘምኖ ጊዜውን የዋጀ አሰራር በመከተል የተጣለበትን አደራ ለመወጣት ኦፊሰሩ ዝግጁ እንዲሆን አሳስበዋል።
ስልጠና አንዱ የተቋም ግንባታ መሳሪያ በመሆኑ የተሰጠው ስልጠና ተግባራዊ መደረግ እንዳለበትና ስልጠና ተግባራዊ መሆኑ በተልዕኮ ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።
የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በበኩላቸው የሀገራችንና የከተማችን ወቅታዊ ሁኔታ በመዳሰስ የተቋማችን ኦፊሰሮች ጥንካሬና ክፍተቶችን በመለየት ኦፊሰሮች ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጡ እና በስነ-ምግባር የታነፁ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ የአቅም ግንባታ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።
ምክትል ስራ አስኪያጁ አክለው እንደተናገሩት ሰው ክቡር ነው ብሎ በሰብዓዊነት የሚሚያገለግል ኦፊሰር ለመፍጠር በዚህ የስልጠና ሂደት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ስልጠና ተሰቷል፤ በዚህም ይህንን እና ሌሎች ስልጠናዎችን መሰረት በቀጣይ በተግባር ልታውሉ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ዋና ስራ አስኪያጁ ለሰልጣኞች የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የአሰራር ክፍተቶችን በመድፈን እና በተሻለ ማንነት እንዲሁም ህብረተሰቡን በቅን በአገልጋይነት ስሜት እንዲያገለግሉ አሳስበው ስልጠናውን ላጠናቀቁ የሰባተኛ ዙር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments