ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ዙሪያ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ

ባለስልጣኑ በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ

               21/05/2018 ዓ.ም
              ** ሰንዳፋ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን  ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለ7ኛ ዙር ነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለተሻለ ተልዕኮ ዝግጁ ለማድረግ  በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ የተዘጋጀ ስልጠና የባለስልጣኑ ዳይሬክተሮችና የስልጠናው አስተባባሪዎች በተገኙበት በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል።

በባለስልጣኑ  የስነ -ምግባር እና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ የስልጠናዉን ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን ስልጠናው ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሩን የስራ ስነ-ምግባር በመላበስ የመፈፀምና የማስፀም አቅሙን ለማሳደ ያለመ መሆኑ ገልፀዋል።

በግምገማዊ ስልጠናው ተልእኮን ከአመራር ተቀብሎ ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ፣ ከሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች ፣ ከህግ ተፈጻሚነት ጋር በተያያዘ ፣ ከሰብአዊ መብት አጠባበቅ አንጻር ስላሉ ክፍተቶች ፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አኳያ ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

በዕለቱ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር132/2014 ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ቁጥጥር ፍተሻና ብቃት ማረጋገጥ ሥርዓት መማሪያ ጥቁር 163/2017 እና የአተገባበር ማንዋል ላይ የተቋማት የአደጋ ደህንነት ማካተትና  ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ዘላለም አንለይ ስልጠና ተሰጥቷል ።

ከሰልጣኙ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኝ  ኦፊሰሮች በስልጠናው ራሳቸውን የተመለከቱበትና   ህብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል ዝግጁ የሚያደርግ እውቀቶችን የቀሰሙበት እንደሆነ ገልጸዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄና ሀሳቦች ዙሪያ በባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና ሰብአዊ መብትን ከማስጠበቅ አንጻር ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጣ እና በመግባባት ግምገማዊ ስልጠናው ተጠናቋል።

ዘገባው፦ የባለስልጣኑ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments