የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ልምድና ተሞክሮውን ለአቻ ተቋማት አጋራ
የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ልምድና ተሞክሮውን ለአቻ ተቋማት አጋራ
19/05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ከሰተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ለመንገዶች ባለስልጣን እና ለአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስራዎቹን የተመለከተ ልምድና ተሞክሮውን አጋራ።
በልምድ ልውውጡ የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ የምስራች ግርማ ስለ ደንብ ማስከበር ስልጣንና ተግባር፣ሀላፊነትና የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቱ የስራ ክፍሉን
መዋቅር፣ አደረጃጀትና ዝርዝር ስራዎችን ገለፃ አድርገዋል።
የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት በተዋቀረ አጭር አመታት ከባለስልጣኑ አመራሮች ጋር በመግባባት መስራት በመቻሉ የተሻለ የሚዲያ ግንኙነትና የገፅታ ግንባታ ስራዎች በተቋሙ የድምፅና የምስል ስቱዲዮ በማስገንባት በሜንስትሪሚንግ እና በሶሻል ሚዲያዎች የደንብ መተላለፎችን ግንዛቤ በመፍጠር እንዲቀነሱ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ተቋሙን ተግባራትና ሀላፊነት ሁሉም የኮሙኒኬሽን አማራጮች በመጠቀም ከተቋሙ አመሮች በመነጋገርና በማቀድ ለማስተዋወቅና የህብረተሰቡን አጋርነት ለማረጋገጥ ከተፅኖ ፈጣሪ አርቲስቶች፣ ቲክቶከሮችና በጎ ፍቃደኞች ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።
በመድረኩ የተገኙት አቻ ተቋማት ጋር የተቋሞቻቸው ልምድና የስራ ተሞክሮ በመግለፅ የተሻለ ተሞክሮአቸውን በመድረኩ አቅርበዋል።
ተቋማት በአንድላይ የስራ ልምዳቸው እንዲያጋሩ መደረጉ የተሻለ ስራ ወደ ራስ ተቋም በማምጣት ተቋማት የላቀ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ስራ በመስራት ለህብረተሰባችን ጥራት ያለው መረጃ በስፋት ተደራሽ በማድረግና የከተማ አስተዳደሩን አላማ ከግብ ለማድረስ እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
በልምድ ልውውጥ አባላት የባለስልጣኑን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አደረጃጀት፣ የመረጃዎችን አሰናነድ፣ የስቱዲዮ ቀረፃ ስራዋች እና የፕሮዳክሽን ስራዎች ተመልክተዋል ።
በመጨረሻም ተመጋጋቢ ተግባራት ያላቸው መንገዶች ባለስልጣን፣የደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና ውሀና ፍሳሽ ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬቶች በቀጣይ በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።
መረጃው :- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments