ከአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ባለው እድገትና ዘመናዊነት መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎችን ለተቋም ሰራተኞች መስጠት አስፈለጊ መሆኑ ተገለፀ
ከአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ባለው እድገትና ዘመናዊነት መሰረት ያደረጉ ስልጠናዎችን ለተቋም ሰራተኞች መስጠት አስፈለጊ መሆኑ ተገለፀ
13/5/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የሚሆኑ የሰባተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲገቡ።
ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣ በባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች እና በፓሊስ ዩንቨርስቲው ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በስልጠና መክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ስልጠናው በአግባቡ በመውሰድ ከብልሹ አሰራር እራሳቸውን ማፅዳት እንዳለባቸውና ለአዲስ አበባ ከተማ የሚመጥን የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰር ለመሆን የንደፈ ሀሳብ እና የአካል ብቃት ስልጠና መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
አያይዘውም ከአዲስ አበባ ከተማ እየታየ ባለው እድገትና ዘመናዊነት መሰረት ስልጠናዎችን ለተቋም ሰራተኞች መስጠት አስፈለጊ በመሆኑ የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና እርምጃ ለመውሰድ ስራዎች ሲሰሩ በጥብቅ ዲሲፒሊን በተግባቦትና በዕውቀት ለይ በመመስረት እንዲሰሩ ስልጠናው በተለያዩ ዙሮች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ስልጠናው በሀገር ወዳድነት፣ በግጭት አፈታት ፣በመረጃ አያያዝ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በተግባቦት ክህሎት ፣ የእሳት አደጋን በመከላከል እና የአካል ብቃት ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ተመልክቷል ።
በመርሀ ግብሩ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩንቨርስቲው ከባለስልጣኑ ጋር በመተባበር የሚሰጠውን ስልጠና የዩንቨርስቲውን ህግና ደንብ በማክበር ስልጠናው በትኩረት መውሰድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።
ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት አስላልፈዋል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments