ባለስልጣኑ ከስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ ከስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ
09/05/2018 ዓ.ም
**ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በስድስተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የወታደራዊና የስነ ምግባር ስልጠና የማጠቃለያ ውይይት የባለስልጣኑ አመራሮች በተገኙበት አካሂደዋል ።
በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ከተማችን የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ፣ የአፍሪካ መዲና እና ዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መቀመጫ በመሆኗ በከተማችንን እየታየ የሚገኘውን እድገት ለማስቀጠልና ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በከፍተኛ ተነሳሽነት ስራዎችን በማከናወን የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል የተገልጋይ እርካታን በማሳደግ በላቀ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል ።
ተቋሙ ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን ፣ በሰው ኃይል ራሱን በማደራጀት ፣ የተቋም ግንባታ ስራውን በማጠናከር እንዲሁም ለኦፊሰሩ እና ለስራ መሳካት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በማሟላት በከተማ አስተዳደር የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት በርካታ ተግባርት እናከናወነ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።
አክለውም ስልጠናው የረጅም ጊዜ ዕውቅና ባለው ዩኒቨርስቲ የብዙ ጊዜ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች በመስጠቱ ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ፍጹም ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው ገልጸዋል ።
በመድረኩ የተገኙት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከተማችንን ያለችበትንና እየሄደችበት ያለውን እድገት የሚመጥን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚችል ብቁ አመራርና ኦፊሰር ለመፈጠር የተሰጠው ስልጠና ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል።
አክለውም እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና ከተማችንን የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ሰላምና ጸጥቷ የተጠበቀ ለነዋሪዎቿ እና ለእንግዶች ምቹ በማድረግ በስነምግባር የታነጸ ኦፊሰር በመገንባት የተሰጠንን ተልዕኮ በውጤት ለመወጣት መሆኑን ገልጸዋል ።
ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments