ብቃት ያለው የደንብ አስከባሪ ኦፊሰርን ለመገንባት በጥልቀት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
ብቃት ያለው የደንብ አስከባሪ ኦፊሰርን ለመገንባት በጥልቀት እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
06/05/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ **
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በሰንዳፋ የፌደራል ፓሊስ ማሰልጠኛ ተቋም እየሰጠ የሚገኘውን የአቅም ግንባታ ስልጠና በማገባደድ ላይ እንደሚገኝ የባለስልጣኑ የስልጠናና ቅድመ መከላከል ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ገለፁ።
ተቋሙ የከተማዋን መዘመንና ልማቷን በሚያስጠበቅ ደረጃ የደንብ መተላለፍን የሚቆጣጠርና የሚከላከል ኦፊሰርን ለማብቃት የንድፈ ሃሳብና የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠናን ለነባር ኦፊሰሩ እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የሀገር ፍቅር፣ የባህርይ፣ የተግባቦት ክህሎትና ስራዎችን በቴክኖሎጂ መፈፀም የሚያስችል የተግባር ስልጠናን ሲሰጥ ቆይቶ ከዚህ በኃላ የሁለት ዙር ሰልጣኞች ብቻ እንደሚቀሩት ዘርፍ ኃላፊው ተናግረዋል።
በተለያየ ዙር ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና አጠናቀው ወደ ስራ የተሠማሩ ኦፊሰሮችንም በግምገማዊ መድረክ ስልጠና በማሳለፍ የስራ ተነሳሽነቱ የጎለበተና ዝቅ ብሎ ህብረተሰቡን የሚያገለግል ኦፊሰርን ወደ ህብረተሰቡ ማሰማራት የተቻለ መሆኑን የገለፁት ምክትል ስራ አስኪያዱ፤ በቀጣይ ቴክኖሎጂን በስፋት በመጠቀም የከተማዋን የደንብ መተላለፍ በብቃት በመከላከልና በመቆጣጠር ባለስልጣኑ በ2022 ዓ.ም እውን ለማድረግ የወጠነውን ራዕይ ከዳር ለማድረስ በፍፁም ተነሳሽነትና ሞራል እየሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
ዘገባው:- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኔኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments