በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6...

image description
- In code inforcement    0

በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ ።

በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ ።

                 02/05/2018 ዓ.ም
                 **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን እና የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር ግምገማዊ የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በከተማችን ዘላቂ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነበት ሁኔታዎችን በመፍጠር  አለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችና ኮንፈርንሶች እንዲሁም በአደባባይ የሚከበሩ የሃይማኖትና ህዝባዊ በዓላት  ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ያለምንም የጸጥታ ችግር ተከብሮ እንዲጠናቀቅ መቻሉን ነው ።

የሰላም ኮንፈረንሶችን በማካሄድ ህብረተሰቡን በከተማዋ  ሰላምና ጸጥታ ዙሪያ በማሳተፍና በማወያየት የሰላም ባለቤት በማድረግ  በከተማችን የወንጀል ምጣኔ ተያያዥ ህገወጥ ተግባራት እንዲቀንሱ ማድረግ መቻሉን ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ገልጸዋል ።

ደንብ ማስከበር መሬት ባንክ የገቡ መሬቶችን በአግባቡ በመጠበቅና በመከላከል የመሬትን ወረራን መቶ መቶ መቆጣጠር የቻለበት መሆኑንና ሌሎች በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎችን እንዲቀንሱ በማድረግ በርካታ ተግባራት ማከናወኑን ገልጸዋል ።

አክለውም ሁለቱ ተቋማት የጸጥታ ሀይሉን በማቀናጀትና በማስተባበር ያከናወኑት ውጤታማ ተግባር በቀጣይም አጠናክሮ በማስቀጠል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት  ባለፉት ስድስት ወራት የተቋም ግንባታ ስራን በማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት በማስጀመር ስራዎችን ዘመናዊና ዲጅታል በማድረግ  ፣የሥልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በስፋት በመስራት እና በከተማዋ የሚታዪ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በከተማችን የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፎች 87.6% እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን ነው፡፡

አክለዉም በቀጣይ ስራዎችም ስኬትን ለማስቀጠል ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ
በአደረጃጀት የተገኘውን ውጤት አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲሁም ቅንጅታዊ ስራዎችንም በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2018 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክተር ኮለኔል አድማሱ ተክሌ ቀርቧል።

ባለስልጣኑ ከተሰጠው ተልዕኮ ጎን ለጎን የበጎ ፍቃድ ሰው ተኮር ሰራዎችን በማከናወን አስራ ስድስት(16) የአቅመ ደካማ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ለባለቤቶቹ ማስረከቡ በሪፖርቱ ተካቷል ።

ከደንብ ተላላፊዎች ቅጣት እና ከተወረሱ ንብረቶች ጨረታ ሽያጭ እስከአሁን ባለው ከ206 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ ፋይናንስ ገቢ ማስገባት መቻሉ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮን የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የእቅድና በጀት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማስረሻ ሀብቴ ቀርቧል።

ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ  የሰላም ሰራዊትና ሌሎች የጸጥታ አደረጃጀቶችን በአደረጃጀትና በግብዓት በማጠንከር የጸጥታ አጋዥ ሃይል እንዲሆኑ በመደረጉ ሰላምና ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎችን አስቀድሞ በመለየት በከተማችን የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉ በሪፖርቱ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በመድረኩ የተሳተፉ አመራሮችና ዳይሬክተሬቶች በቀረበው በእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ሀሳብናና ጥያቄዎች አቅርበው ከመድረኩ ምላሽ ተሰጥቶበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ የቢሮው ዋና ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አስቀምጠዋል ።

በተጨማሪም በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የጸጥታ ስራዎች ማስፈጸሚያ እቅድ ቀርቧ ውይይት ተካሂዷል ።

ዘገበው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳሬክቶሬት ነው፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments