የባለስልጣኑ ስድስተኛ ዙር የወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ሰነዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ማሰልጠኛ መግባታቸው ተገለፀ
የባለስልጣኑ ስድስተኛ ዙር የወታደራዊ እና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ሰነዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርሲቲ ማሰልጠኛ መግባታቸው ተገለፀ
01/5/2018 ዓ.ም
** ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የስድስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአካል ብቃትና እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ለመውሰድ ገቡ።
ሰልጣኞቹ ወደ ማሰልጠኛው ሲደርሱ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጠን ምክትል ስራአስኪያጅ በአቶ ንጋቱ ዳኛቸው እና በባለስልጣኑ የስልጠና አስተባባሪዎች እና በፓሊስ ዩንቨርስቲው ማህበረሰብ አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።
በስልጠና መክፈቻ መርሀ ግብሩ በስልጠና ማዕከል በመገኘት ለሰልጣኝ ኦፊሰሮች እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ምክትል ስራአስኪያጅ ስልጠናው አሁን ላይ ከተማችን አዲስ አበባ የሚመጥን የደንብ መተላለፎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አቅም ለማሳደግ እና ከህብረተሰቡ ጋር በስራ ዲሲፒሊን ተግባብቶ ለመስራት አቅም የሚፈጥር መሆኑ ገልፀዋል።
ስልጠናው በሀገር ወዳድነት፣ በግጭት አፈታት ፣በመረጃ አያያዝ፣በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ በተግባቦት ክህሎት ፣ የእሳት አደጋን በመከላከል እና የአካል ብቃት ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ተመልክቷል ።
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸዉ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ዩንቨርስቲው ከባለስልጣኑ ጋር በመተባበር የአቅም ግንባታ ስልጠናው በዲሲፕሊን ሊወሰድ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ሥልጠናው ለ10 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይና በመግለፅ ሰልጣኞች ስልጠናው በዲሲፕሊን፣በንቃትና በብቃት እንዲከታተሉ መልዕክት ተላልፏል ።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments