ትውልድን በስነ-ምግባር የመገንባትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በእውቀት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ
ትውልድን በስነ-ምግባር የመገንባትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በእውቀት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ
27/04 /2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለአምስተኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰልጣኝ ነባር ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል ።
በትውልድ የስነምግባር ግንባታ ለነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ለተሻለ ተልዕኮ ለማብቃት የተዘጋጀው የግምገማዊ ሰነድ የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደመስቀል ቀርቧል ።
የደንብ ማስከበር መዋቅር በአዋጅ በደንብ እና መመሪያ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደርጉትን ችግሮች በመለየት የመፍትሔ አቅጣጫ በማስቀመጥ እና መፍትሔዎች ላይ መግባባት ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል ።
በመድረኩ ተቋሙን ከስነ-ምግባር አኳያ በጥንካሬ እና በድክመት የሚታዩና ነባራዊ ሁኔታ ፣ የደንብ መተላለፍ መንስኤና ተፅዕኖ ፣ ተግዳሮትና የመፍትሄ ኃሳቦች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦች በጥልቀት የያዘ ሰነድ በማቅረብ ግምገማዊ ስልጠናው ተሰጥቷል ።
ስልጠናውን የሚወስዱ የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስነምግባርና ብልሹ አሰራር ፤ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ የሰብዓዊ መብት አያያዝን እና የስምሪት አሰጣጥ ችግሮችን በአግባቡ በመረዳት ለቀጣይ በተቋሙ ለሚሰጠው ተልዕኮ ዝግጁ መሆን እንደሚገባ በመድረኩ ተመልክቷል ።
በመጨረሻም ከሰልጣኞች ለተነሱ ሀሳቦችና ጥያቄዎች በባለስልጣኑ ዳይሬክተሮች እና የስልጠና አስተባባሪዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ ተቋሙ ለሚያደረገው ትውልድን በስነ-ምግባር የመገንባትና ብልሹ አሰራርን የመከላከል ስራ በእውቀት በመታገዝ የተሻሉ ስራዎች ሊሰሩ እንደሚገባ የጋራ መግባባት በመፍጠር ስልጠናው ተጠናቋል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments