ባለስልጣኑ ከሽፍት አስተባባሪዎች ፣ ሽፍት መሪዎች እና ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር ያደረገውን የአገልግሎት አሰጣጥ ግምገማ መድረክ ማጠቃለያ ውይይት አካሄደ
ባለስልጣኑ ከሽፍት አስተባባሪዎች ፣ ሽፍት መሪዎች እና ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር ያደረገውን የአገልግሎት አሰጣጥ ግምገማ መድረክ ማጠቃለያ ውይይት አካሄደ
18/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወቅታዊ የተቋቋሙ ጥንካሬዎች እና የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ከሽፍት አስተባባሪዎች፣ሽፍት መሪዎች እና ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር በማዕከል፣በክፍለ ከተማ እና በ119 ወረዳዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ሲካሄድ የቆየው የግምገማ መድረክ በዛሬው እለት የማጠቃለያ ውይይት አካሂዷል ።
በውይይቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ተቋሙ ወደፊት የሚጠበቁበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በከተማዋ በከተቋማችን ምትፈልገው አገልግሎት በተሰጠውን ተልዕኮ ልክ በአግባቡ ለመወጣት ከአመራሩ እና ከኦፊሰሩ የአሰራር ለውጥ ማምጣት የሚጠበቅ መሆኑ ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ ህብረተሰቡን በሙያዊ ስነ ምግባር ማገልገል እንዲቻል አመራሮቹና ሰራተኞቹ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሰንዳፋ እና አዳይቱ ካምፖስ ስልጠናዎች መሰጠታቸው እና አሁንም በዙር እየተሰጠ መሆኑ ገልፀው በስልጠናው የሚፈለገው ውጤት ለማምጣት የአመራሩ በየዕለቱ ክትትል ማድረግ እንደሚጠበቅ ገልፀዋል ።
የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ የተሰጠን ተልዕኮ ከመፈጸም አንጻር የወረዳ አመራሮች ለሽፍት አስተባባሪዎች ፣ ለሽፍት መሪዎች እና ለፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ተልዕኮ ሰጥተን ተልዕኮውን በጥንካሬና በድክመት በመገምገም የሰጠነውን ተልዕኮ ቆጥረን መረከብ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በእለቱ ከከተማ እስከ ወረዳ በግምገማው የተለዩ የስነ-ምግባርና እና የአሰራር ክፍተቶች እና ተጠያቂ የተደረጉበት መረጃ በሰነድ የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ በአቶ ተስፋሁን አሉላ ቀርቧል።
በመድረኩ የክፍለ ከተማ አመራሮች በየክፍለ ከተማቸው የተለዩት ችግሮች በወረዳና በግለሰብ ላይ በማሳረፍ ተጠያቂ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል
የግምገማ መድረኩ ተሳታፊዎች ተቋሙ በአዋጅ፣በደንብና መመሪያ የተሰጡትን ተልዕኮዎችና ሀላፊነቶች በአግባቡ እንዲወጣ የሚያደርጉትን ችግሮች በመለየት ማስተካከያ መደረጉ የስራ ዲሲፕሊን በተጨማሪ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም እንደሚያጎለብት ተናግረዋል።
በማጠቃለያ መድረኩ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን፣ለስራ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር፣ የሌብነት እና ብልሹ አሰራር ምጮችን መለየት ተጠያቂ የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ጠቁመዋል።
በዕለቱ የሰለጠኑ የስራ መሪዎችና ኦፊሰሮች በስልጠናው ያመጡት ለውጥ በመገምገም ተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መቀበል እና መፈፀም የማይችል አመራርና ኦፊሰር ከተቋሙ ጋር መቀጠል የማይችል መሆኑ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በግምገማው መድረክ ላይ የተነሱ ችግሮች ተለይተው በእቅድ በመያዝ መፍትሄ እንደሚቀመጥላቸው በመግለፅ የቀጣይ የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments