በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ በስልጠና ላይ የነበ...

image description
- In code inforcement    0

በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ በስልጠና ላይ የነበሩ የባለስልጣኑ የአራተኛ ዙር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስልጠና የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ

በኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርስቲ በስልጠና ላይ የነበሩ  የባለስልጣኑ የአራተኛ ዙር የፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የስልጠና የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ
  
          17/04/2018 ዓ.ም
             **ሰንዳፋ**   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በአራተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካል ብቃትናና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና  የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ሰንዳፋ በሚገኘው በኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲ የማጠቃለያ ውይይት ተካሄደ ።

በማጠቃለያ ውይይቱ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ዘርፍ ከፍተኛ እድገት እያመጣችና በዚህ ጊዜ አባይን ገድባ በማጠናቀቅ ታላላቅ ፕሮጀክቶች በመስራት ወደ ከፍታ እየተጓዘች ያለች ሀገር  መሆኗን ጠቁመው አዲስ አበባ ከተማም እንደ ስሟ አበባ ለማድረግ በኮሪደር ልማት ደምቃ እንድትታይ የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ  ያበረከተው አስተዋፅ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በባለስልጣኑ ከፍተኛ  እምነት ስላለው የተለያዩ ደንብና መመሪያዎች እንዲያስተገብር ተልዕኮ በመሰጠት ላይ በመሆኑ በእውቀት ላይ ተመስርቶ በቴክኖሎጅ ዘምኖ ጊዜውን የዋጀ አሰራር በመከተል የተጣለበትን አደራ ዝግጁ  መሆን እንዳለበት ዋና ስራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።

ተቋሙ ሰራተኞቹን በስልጠና በማብቃት የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማስተግበር ዘመኑን የሚጠይቀው አሰራር  በመከተል  በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን እንደሚከናወን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ።

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ በተሰጠው ስልጠና ኦፊሰሩ በአካልና በአዕምሮ እውቀት አዳብሮ አቅሙን በማጎልበት የከተማ አስተዳደሩን የደንብ መተላለፎች ለመከላከል፣ለመቆጣጠር እና ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ አቅም የሚፈጥር ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ።

ምክትል ስራ አስኪያጁ  የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮቹ  የደንብ መተላለፎች እና ተያይዥ ህገወጥ ተግባራት የመከላከል እና እርምጃ የመውሰድ ስራ ሲከናወን ስነ ምግባር በመላበስና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ  ገልጸዋል ።

የባለስልጣኑ አማካሪ ወ/ሮ አበባ እሸቴ በበኩላቸው  የደንብ ማስከበር ስራዎች ሲሰሩ በእውቀት ላይ በመመስረት እንዲሰሩና የነበሩ ክፍተቶችን ለሙላት በተከታታይ ዙር በኢትዮጵያ ፓሊስ ማሰልጠኛ የአቅም ግንባታ  እና የንደፈ ሀሳብ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው ባለስልጣኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እራሱን በማሻሻል በየጊዜው አስፈላጊ የሆኑና የተለዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በመጨረሻም ዋና ስራ-አስኪያጁ ለሰልጣኞች የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሩ የአሰራር ክፍተቶችን ሳይፈጥሩ ህብረተሰቡን እንዲያገለግሉ አሳስበው ስልጠናውን ላጠናቀቁ የአራተኛ ዙር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።

ዘገባው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments