ባለስልጣኑ ለአራተኛ ዙር ሰልጣኞች በትውልድ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ለአራተኛ ዙር ሰልጣኞች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ባለስልጣኑ  ለአራተኛ ዙር ሰልጣኞች  በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ዙሪያ ግምገማዊ ስልጠና  ተሰጠ፡፡       
                  
        16/04/2018 ዓ.ም
         **ሰንዳፋ**
   
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለአራተኛ ዙር ነባር ፓራ ሚሊተሪ  ኦፊሰሮች የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ አመራርና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ  ሰንዳፋ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል።

የዕለቱን መድረክ የከፈቱት የባለስልጣኑ ምክትል ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ሰልጣኝ ኦፊሰሮች የሚሰጣችሁ ስልጠና በአግባቡ እንድትከታተሉ የተቋሙን ራዕይ እና ተልዕኮ እንድትወጡ  ሲሉ ተናግረዋል።

የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል ለአራተኛ ዙር  የአካል ብቃትና ንድፈ ሀሳብ ስልጠና አመራርና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ  ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማዊ ስልጠና ሰተዋል።

ሰልጣኞቹ በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን እውቀት ከብልሹ አሰራር በፀዳ መልኩ ስነ_ምግባር ትህትናን በመላበስ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋ።
  ተቋሙ እየሰጠ ያለውን የንድፈ ሀሳብ እና የአካል ብቃት ስልጠና ለቀጠይ ስራቸው ትልቅ ግብዓት እንደሆነላቸው ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም  ሰልጣኞች ላነሱት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በመድረክ መሪዎቹ ተሰጥቶ መድረኩ ተጠናቋል፡፡ 

ዘገባው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ  ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments