የምንሰራበት ተቋምና የስራ ድርሻ በመውደድ ህብረተሰባችን ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ
የምንሰራበት ተቋምና የስራ ድርሻ በመውደድ ህብረተሰባችን ማገልገል እንደሚገባ ተገለፀ
ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የወርቃማ ሰኞ የአብሮነት መድረክ የተቋሙ አመራሮች ሰራተኞች በተገኙበት በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል ።
በመድረኩ ከባለስልጣኑ ግንዛቤ ማስጨበጥ ዳይሬክቶሬት አቶ የኔዓለም ሙሉ ጀንበሬ "ስለ መሪነት" leadership ሰነድ በማቅረብ ዕውቀትና ተሞክሮ አጋርተዋል።
መሪነት/leadership ምንነት፣ የመሪነት መገለጫዎች፣ በመሪነትና በማስተዳደር/management መካከል ስላለ ልዩነትና አንድነት በሚሉ ነጥቦች ላይ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የባለስልጣኑ ዋና ሰራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሰራተኛው የሚሰራበት ተቋምና የስራ ድርሻ በመውደድ ህብረተሰባችን ማገልገል እንደሚገባ በመግለፅ በሳምንቱ ስለተመዘገቡ መልካም ውጤቶች እና የቀጣይ ሳምንት የስራ አቅጣጫ በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል ።
መረጃው፦ የባለስልጣኑ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments