የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ
የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የቅድመ መከላከልና የግንዛቤ ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ
10/04/2018 ዓ.ም
**አዲስ አበባ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በወቅታዊ የተቋሙ ጥንካሬዎች እና አንዳንድ የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ አስራ አንዱም ክፍለ ከተማ በአራት ክላስተር የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ከአዳይቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ ሽፍት አስተባባሪዎች ፣ሽፍት መሪዎችና ነባር ኦፊሰሮች ጋር ግምገማዊ የውይይት መድረክ አካሂዷል ።
የውይይቱ ዓላማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን መዋቅር ተቋሙ በአዋጅ ፣ በደንብና መመሪያ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ እንዳይወጣ የሚያደርጉትን ችግሮች በመለየት በመፍትሔው ላይ መግባባት እንዲቻል እና ስነምግባር የተላበሰ ኦፊሰር ለመገንባትና ብልሹ አሰራርን ለመታገል መሆኑ በመድረኮቹ ተገልጿል ።
የመድረኩ ተሳቲፊዎች የአገልግሎት አሰጣጣችን በማሻሻል ጥንካሬዎቻችን በማስቀጠል የሚታዪ ክፍተቶችን በመሙላት የተቋም ገጽታ ግንባታ ስራን በማጠናከር እንዲሁም የሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመታገል በቀጣይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ጠንክረው ለመስራትና የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እና የደንበኞችን እርካታ ማሳደግ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለይቶ በማሻሻል ብሎም በቀጣይ የቅድመ መከላከል ስራዎችን በማጠናከር ማህበረሰቡ የደንብ መተላለፍ እንዳይፈጽምና እንዲረዳ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት የደንብ መተላለፍን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ ተገልጿል ::
መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments