የአራተኛ ዙር ሰልጠኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰ...

image description
- In code inforcement    0

የአራተኛ ዙር ሰልጠኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ማሰልጠኛ በሰላም ገብተዋል

የአራተኛ ዙር ሰልጠኝ  ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ወደ ማሰልጠኛ በሰላም ገብተዋል

             07/04/2018 ዓ.ም
              **ሰንዳፋ**      

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ የተወጣጡ ከ600 በላይ የአራተኛ ዙር የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና ሰልጠኝ  ነባር የፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮችና አመራሮች ወደ ሰንዳፋ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በሰላም ገብተዋል።

ወደ ማሰልጠኛው እንደደረሱ በባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ፣በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር የአቅም ግንባታ የስልጠና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብና ከስልጠና አስተባባሪዎች ጋር አቀባበል ተደርጎላቸዋል ።

ስልጠናውን ያስጀመሩት የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ደንብ ማስከበር አቅሙን በየጊዜው በማሳደግ ስራዎቹን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ  እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎችን ለአመራሩ እና ለኦፊሰሩ በመስጠት የአቅም ግንባታን ስራ  በመሰራት ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል ።

አክለውም አስከአሁን ከሶስት ሺህ በላይ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሰንዳፋ እና አደይቱ ካምፖስ የአቅም ግንባታ ስልጠናውን ብቃት በመወጣት ማጠናቀቃቸውን የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ ገልጸዋል ።

አክለውም የሚሰጠውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል የግቢውን  ህግና ደንብ በማክበር ሰልጣኞች ስልጠናውን በቂ እውቀት አግኝተው ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአመራር የአቅም ግንባታና የስልጠና ማዕከል መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ፍቃዱ ጌታቸው ለሠልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ሰልጣኞች ስልጠናውን የግቢውን ህግ በማክበር በትኩረት መውሰድ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል ።

የንድፈ ሀሳብ  እና የአካል ብቃት ሥልጠናው ለ10 ተከታይ ቀናት  እንደሚቆይና በቀጣይ ዙሮችም ለተቀሩት ነባር ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ስልጠናው እንደሚቀጥል ተገልጿል ።

መረጃው:- የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments