የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከ...

image description
- In code inforcement    0

የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ ጋር የእንጠያየቅ መድረክ አካሄደ::

የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት  ከህብረተሰቡ ጋር የእንጠያየቅ መድረክ አካሄደ::

7/4/2018 ዓ/ም
     **አዲስ አበባ**

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በልደታ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በክፍለ ከተማው ስር ባሉት 10 ወረዳዎች ከተውጣጡ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የእንጠያየቅ መድረክ አካሄዷል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ  የዛሬው የእንጠያየቅ መድረክ ዋና ዓላማ በአስራሮች ላይ ያልተደረሰባቸውን እንዲሁም በተቋማችን  መፈታት ኖሮበት  ያልተፈቱ የህዝብ ጥያቄዎችን በመውሰድ  ችግሩን በጋራ ለመፍታት እንደሆነ ገልፀዋል።

በመድረኩ በክፍለ ከተማው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከህብረተሰቡም በርካታ ሃሳቦች ተነስተዋል በተለይ ተቋሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ የህዝብ ጥያቄ የሆኑት ህገ ወጥ ተግባራትና የደንብ ጥሰቶች እንዳይፈፀሙ ከመከላከል አንፃር  ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት ህብረተሰቡን በማሳተፍ አበረታች ውጤቶችን እያመጣ እንደሆነ  ተመላክቷል።

በክፍለ ከተማው  የደረቅና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ፣ ህገ ወጥ የጎዳና ላይ ንግድና ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ የእንስሳት እርድ የመሳሰሉ የደንብ መተላለፍ ተግባራት ስሚስተዋሉ ፅ/ቤቱ በልዩ ትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ከተሳታፊዎች ሃሳብና አስተያየቶች ተነስተዋል።

ከህብረተሰቡ በተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ላይ የልደታ ክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ኢቲቻ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተውበት መድረኩ ተጠናቋል።

መረጃው:- የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ /ቤት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments