ባለስልጣኑ ከሶስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊ...

image description
- In code inforcement    0

ባለስልጣኑ ከሶስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ

ባለስልጣኑ ከሶስተኛ ዙር ሰልጣኝ ነባር ፖራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች ጋር የማጠቃለያ ውይይት አካሄደ    

           07/04/2018 ዓ.ም
              ****ሰንዳፋ****    

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለነባር ፓራ ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በሶስተኛ ዙር ሲሰጥ የቆየውን የአካል ብቃትናና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና የማጠቃለያ ውይይት የባለስልጣኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አካሂደዋል ። 

በመድረኩ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ሀገራችን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊና በፖለቲካዊ ከፍተኛ እድገት እያመጣች ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሃን እየተጓዘች እንደመሆኗ ተቋማችን በከተማ አስተዳደሩ የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ በመወጣት እያስመዘገበ የሚገኘውን ውጤት በቴክኖሎጂ አጠናክሮ አገልግሎት አሰጣጡን አሻሽሎ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል ። 

ተቋሙ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ጋር  በመተባበር የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን በማስተግበር ራሱን በማዘመን ላይ እንደሚገኝና በአጭር ጊዜ ውስጥ ስራውን በማጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ስራዎችን እንደሚከናወን ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል ። 

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው ከተማችንን ያለችበትንና እየሄደችበት ያለውን እድገት የሚመጥን የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ መወጣት የሚችል ብቁ አመራርና ኦፊሰር ለመፍጠር የተሰጠው ስልጠና ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል ። 

አክለውም የተሰጡት ስልጠናዎች ሀገር ወዳድነትን የሚጨምሩ ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ወቅቱን የጠበቀ ስራ ለማከናወን የሚያግዙ ፣ የተግባቦት ክህሎትን የሚያሳድጉ ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን የሚያጠናክር እንዲሁም ስነምግባር እንድንላበስና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ህብረተሰቡ በቀናነት ለማገልገል የሚያግዝ ነው ብለዋል ። 

የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ የተሰጠው ስልጠና ከፍተኛ እውቅናና የበርካታ ጊዜ ልምድ ባለው ዩኒቨርስቲ በመሰጠቱ በቀጣይ ለምናከናውነው ተግባራት እና የሚሰጠንን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በቂ ስንቅ የሚገኝበት መሆኑን ተናግረዋል ። 

በከተማዋ የሚስተዋሉ የደንብ መተላለፍ ተያይዥ ህገወጥ ተግባራት የመከላከል እና እርምጃ የመውሰድ ስራ ሲከናወን ስነ ምግባር በመላበስና ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሊሆን እንደሚገባ የባለስልጣኑ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ከፍያለው ታደሰ ገልጸዋል ።

ለተልዕኮ አፈጻጸም መሳካት አመራርና ኦፊሰሩን በማብቃት በየጊዜው ወቅቱን የጠበቁ ስልጠናዎች እየተዘጋጁ እንደሚሰጡ ዋና ስራ አስኪያጁ ገልጸው ስልጠናውን ላጠናቀቁ የሶስተኛ ዙር ኦፊሰሮች የቀጣይ የስራ ስምሪት ሰጥተዋል ። 

መረጃው:- የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments