ባለስልጣኑ ለሦስተኛ ዙር የሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሰልጣኞች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል በተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ
ባለስልጣኑ ለሦስተኛ ዙር የሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ሰልጣኞች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል በተመለከተ ግምገማዊ ስልጠና ሰጠ
06/04/2018 ዓ.ም
** ሰንዳፋ**
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ለሦስተኛ ዙር ከ600 በላይ የአካል ብቃትና የንድፈ ሀሳብ ሰልጣኝ አመራርና ፓራ-ሚሊተሪ ኦፊሰሮች በትውልድ ስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና በመከላከል ዙሪያ ሰንዳፋ በሚገኘው የፌደራል ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ ግምገማዊ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ እና የቁጥጥርና እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወልደ መስቀል ተቋሙን ከስነ-ምግባር አኳያ በጥንካሬ እና በድክመት የሚታዩና ነባራዊ ሁኔታ ፣ የደንብ መተላለፍ መንስኤና ተፅዕኖ ፣ ተግዳሮትና የመፍትሄ ኃሳቦች እንዲሁም ሌሎች ነጥቦች በጥልቀት የያዘ ሰነድ ላይ መሰረት ያደረገ ግምገማዊ ስልጠና ተሰጥቷል።
ከቀረበው ሰነድ በመነሳት ፈጻሚዎች ከቅርብ ኃላፊ ጋር ስላለው መልካም ግንኙነት፣ በሚፈጠሩ የመናበብ ክፍተት፣ ደንብ በማስከበር ሂደቱ ላይ መወሰድ ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ስለሚገጥሙ ተግዳሮቶች፣ ብልሹ አሰራርን የሚጠየፍ እና በስነ-ምግባር የታነፀ ኦፊሰር ከመፍጠር አንጻር መወሰድ ስለሚገባቸው የመፍትሄ ሀሳቦች ተመላክተዋል።
በመድረኩ የባለስልጣኑ የቁጥጥር ክትትል እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም
ወ/መስቀል በደንብ ቁጥር 150/2015፣ 167/2016፣180/2017 እና የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ነባራዊ ሁኔታ አስገንዝበዋል።
በተጨማሪም በመድረኩ ከአደጋ ስጋት ቅነሳ አመራር ኮሚሽን አቶ ጋሻሁን ካሳዬ በአደጋ ስጋት ደህንነት ደንብ ቁጥር 132/2014 ስልጠና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በመድረኩ ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም አገልግሎት አሰጣጥን በሚገባ በማስተካከል ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ስነምግባር በመላበስ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አክለውም ሰልጣኞች ተቋሙ እየሰጠ ያለውን የንድፈ ሀሳብ እና የአካል ብቃት ስልጠና ጥሩ እና በኦፊሰሩ ላይ ያለውን የክህሎት ችግር ፈቺ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።
በመጨረሻም ቀጣይም ስልጠናው በታቀደለት ጊዜ አመራሩና ኦፊሰሩን ለማብቃት ወቅቱን የጠበቀ ስልጠናዎች እየተዘጋጁ የሚሰጥ መሆኑን ተገልፆ ከመድረኩ ለተነሱት ሀሳብ እና አስተያየት የባለስልጣኑ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ እዮብ ከበደ፣የቁጥጥር እርምጃ አወሳሰድ ዳይሬክተር አቶ ግሩም ወ/መስቀል እና ከአደጋ ስጋት ቅነሳ አመራር ኮሚሽን አቶ ጋሻሁን ካሳዬ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ።
ዘገባው ፡-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ነው ።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments