በደንብ ቁጥር 180/2017 ደንብ ላይ የግንዛቤ...

image description
- In code inforcement    0

በደንብ ቁጥር 180/2017 ደንብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

በደንብ ቁጥር 180/2017 ደንብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጉለሌ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የወንዞች ዳርቻ ልማት ብክለትን ለመንከባከብ በወጣ የደንብ ቁጥር 180/2017 አስመልክቶ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት  የጉለሌ ክፍለ ከተማ የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ለገሰ  እንደ ደንብ ማስከበር ወደ 14 የሚደርሱ እርከኖች የተቀመጡ ሲሆን በነዚህ ክልከላዎች ደንቡን ያላከበረእና በጣሰ አካል ላይ የሚወሰደው እርምጃና ቅጣቱ ምን እንደሆነ የገንዘብ መቀጮው በቁጥር በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን ከፍተኛው ቅጣት አስከ አንድ ሚሊዮን ብር እንደሚደርስም በመድረኩ ተናግረዋል።

በደንብ ቁጥር 180/2017 የተቀመጡ ክልከላዎች የሚያካትቱት በወንዝና በወንዝ ዳርቻ  ሲያጠብ ፣ፍሳሽ አወጋገድ ፣የአከባቢ ጥበቃና ከመበከል፣ የቆሸሸ ውሃ ወደ ወንዝ መቀላቀል በአጠቃላይ ህገውጥ ድርጊቶች ላይ መሆኑን ገልፀው  ይህ ተግባር እውን እንዲሆን ማህበረሰቡ ተግባሩ እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ፦ https://linktr.ee/aacodeenforcement


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments